በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአውሮፓ የስደተኞት የሰብዓዊ ቀውስ ፍንዳታ ሥጋት


“ከዚያ አልፈው መሄድ ያለመቻላቸውን አያውቁም። ተሰልፈው በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ወደ ሌላ አካባቢ ለመዛወር የሚያስፈልገውን አሟልተው የተገኙ የግድ የሆነ የሚያልፉት ሂደት ይጠብቃቸዋል። ያም ቢሆን ለሁሉም አይደለም። በመሆኑም ተሥፋ መቁረጥ ተደራርቦ ወደ አንዳች የብጥብጥና የግጭት እንቅስቃሴ ሊያመራ ይችላል።” ቪንሰንት ኮችቴል፤ የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮምሽነር የአውሮፓው የስደተኞች ቀውስ የመፍትሄ ጉዳዮች አስተባባሪ።

አውሮፓ በገዛ ራሷ በቀሰቀሰችው የሰብዓዊ ቀውስ ፍንዳታ ቋፍ ላይ ናት፤ ሲል የተባበሩት መንግስታት የሥደተኞች ጉዳይ ፅ/ቤት አስጠነቀቀ። ይሄም ከእጅ ሊወጣና ወደ መጠነ ሰፊ ግጭት ሊያስከትል ይችላል፤ ነው ያለው የመንግስታቱ ድርጅት በማስጠንቀቂያው።

በድርጅቱ ዘገባ መሠረት መተላለፊያ አጥተው መጠለያ ፍለጋ ግሪክ ላይ የሚገኙት ከመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ፈልሰው የመጡ ስደተኞች ቁጥር ሃያ አራት ሺህ ደርሷል።

ከእነኚህም ውስጥ ከመቄዶኒያ ድንበር አቅራቢያ መተላለፊያ አጥተው አንድ ቦታ ተፋፍገው የሚገኙትን ቁጥራቸው ከ8 ሺህ 5 መቶ በላይ የሚደርስ ሰዎች ይጨምራል።

የባልካን አገሮችን አልፎ ወደ አውሮፓ እምብርት በሚያስገባው ኮሪዶር ለማለፍ ሲሞክሩ ድንበሮቹ ላይ ጉዟቸው የተገታውና መተላለፊያ በማጣታቸው ተስፋ የቆረጡ ብዙዎች መሆናቸውን ይናገራሉ።

በአውሮፓ የስደተኞት የሰብዓዊ ቀውስ ፍንዳታ ሥጋት
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:46 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG