በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የክሊንተን ኢሜይሎች፥ አዲሱ ሪፖርትና የቀጠለው ውዝግብ


በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ተፎካካሪ ሂላሪ ክሊንተን /ፋይል ፎቶ/
በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ተፎካካሪ ሂላሪ ክሊንተን /ፋይል ፎቶ/

“ምንም እንኳን የተፈቀደ ቢሆንም፤ ሁለት ራሳቸውን የቻሉ የኢሜል አድራሻዎች መጠቀም ነበረብኝ። አንዱ የግል፤ ሌላው ከሥራ፥ ከኃላፊነቴ ጋር ለተዛመዱ አገልግሎቶች የሚውል። ያን ያለማድረጌ ስህተት ነው። ይቅርታ እጠይቃለሁ። ኃላፊነት የምወስድበት ነው።” በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ተፎካካሪ ሂላሪ ክሊንተን።

የዲሞክራቷን ተፎካካሪ ሴናተር ሂላሪ ክሊንተንን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ እንደ አንዳች ክፉ ጥላ እየተከተለ ሲያጠላ የከረመው የኢሜል አጠቃቀማቸውን የተመለከተ አሰራር ዳግም የዜና ርዕስ እየሆነ ነው።

ጠመመም ያለ መንገድ መከተል የሚወዱት ሂላሪ፥ ይሄው እንደሚሰማው ናቸው። ዛሬ ጥቂት በጎ ያልሆኑ ዜናዎች ገጥሟቸዋል። ከማን ወይም ከየት እንደሆነ ታውቃላችሁ አይደል? አንዳንድ በጎ ያልሆኑ ዜናዎች መጥተዋል። የዋና ተቆጣጣሪው ሪፖርት በጎ ዜና አልያዘላቸውም።
ተቀናቃኛቸው የሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ተፎካካሪም ዶናልድ ትራምፕ

አዲስ ይፋ የሆነው መንግስታዊ ዘገባ፤ “የቀድሞዋ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ለሥራ ጉዳይ የሚላላኳቸውን የኢሜል መልዕክቶች በግል የመረጃ ማከማቻና ማስተላላፊያ ዘዴ በመጠቀም የመሥሪያ ቤታቸውን ደምብ ተላልፈዋል፤” ብሏል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዋና ተቆጣጣሪ በዛሬው ዕለት ይፋ ያደርገዋል ተብሎ የሚጠበቀው ሪፖርት አክሎም፤ የሂላሪ ክሊንተን የኢሜል አጠቃቀም ለአደጋ የተጋለጠ እንደነበር ያትታል።

ይሁንና መርማሪዎቹ እንዳመለከቱት፤ ይህ ክሊንተን የተከተሉት “ለአደጋ የተጋለጠ” ጠቅላላ አሠራር ከእርሳቸው የኃላፊነት ጊዜ የቀደመ ነው።

የሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ተፎካካሪ ዶናልድ ትራምፕ
የሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ተፎካካሪ ዶናልድ ትራምፕ

ክሪስ ሃንስ ያጠናቀረውን ዘገባ አሉላ ከበደ አቅርቦታል ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

የክሊንተን ኢሜይሎች፥ አዲሱ ሪፖርትና የቀጠለው ውዝግብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:35 0:00

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG