ዋሽንግተን ዲሲ —
የሀገሪቱን ችግሮች ለመፍታት የአፍሪካ ህብረት ከፕሬዘዳንት ኦማር አል በሽር (Omar al-Bashir) መንግሥት ጋር ኢትዮጵያ ውስጥ የጠራውን ብሄራዊ ድርድር ፓርቲያቸው እንደሚያከብር አንድ የተቃዋሚ መሪ አስታወቁ።
የቀድሞው የተቃዋሚ መሪና የኡማ (Umma) ፓርቲ ምክትል ፕሬዘዳንት የሰይዲግ አል መሃዲ (Sadig al-Mahdi ልጅ ማርያም አል መሃዲ (Mariam al-Mahdi) ባሁኑ ወቅት ሱዳን ውስጥ እየተካሄደ ያለው ድርድር ለሁሉም አመቺ አይደለም ሲሉ በመተቸት ይቃወማሉ።
ጄምስ ባቲ (James Butty) አጭር ዘገባ አጠናቅሮ የላከውን ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል። ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።