በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ሥምምነት


ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና እና የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ
ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና እና የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ

ተንታኞች እንደሚሉት በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሐምሌ 2018 የተደረሰው የሰላም ሥምምነት፣ ተጫባጭ የሆኑ፣ ጥቂት ጥቅሞችን አስገኝቷል፡፡ የንግድ መስመሮቹ እንደተዘጉ ሲሆን፣ በድንበሩ አካባቢ ያለው ውጥረት አሁንም እንዳለ ነው፡፡ በአካባቢው ተፅዕኖ የማሳደር አቅም ያላቸውና፣ ከኤርትራ ጋር በሚዋሰነው የሰሜን ኢትዮጵያ በምትገኘው የትግራይ ክልል የሚገኙ ሰዎች፣ አስመራ ካለው አመራር ጋር ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር የተዘጋጁ አለመሆናቸውም ይታያል፡፡ ድንበሩ አሁንም ያልተከለለ ሲሆን፣ በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቁ ወታደሮች በአወዛጋቢው የወሰን ክልል ላይ ሰፍረው ይታያሉ፤ ሲመን ማርክስ ከአዲስ አበባ ዘገባ ልኳል፡፡

በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና እና በኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ መካከል የሰላም ሥምምነቱ የተፈጸመ መሆኑ እንደተገነገረ አካባቢ፣ የነበረው ሁኔታ በጣም ጥሩ የሚባል ነበር፡፡ ሥምምነቱን ተከትሎ፣ በሁለት አገሮች መካከል ተቋርጦ የነበረው የስልክ መስመር ተከፈተ፣ በረራዎች ከአዲስ አበባ አስመራ ተደረጉ፣ ሸቃጣ ሸቀጦች ድንበሮችን እያሳበሩ መተላለፍ ጀመሩ፡፡ ይሁን እንጂ፣ ተንታኞች እንደሚሉት፣ ዘላቂውን ሰላም ለማምጣት፣ ትልቁ መሰናክል አሁንም እንደተጋረጠ ነው፡፡

ድንበሩ መከፈት እንደጀመረ፣ በርካታ ኤርትራውያን ወደ ኢትዮጵያ መፍለስና መሰደድ ጀመሩ፡፡ በዚህ የተነሳ ለንግድ መተላለፊያ ክፍት የሆነው ድንበር እንደገና እንዲዘጋ ተደረገ፡፡ እንደ ተንታኞቹ አባባል ፣ በኤርትራና ፣ በሰሜን የትግራይን ክልል ሥልጣኑን በተቆጣጠሩት መካከል፣ ታሪካዊ የሆነ ቁርሾና በዚያም ሳቢያ የተፈጠረ ውጥረት አለ፡፡ በዚያ የተነሳም ለአፍታም ቢሆን፣ ብልጭ ብሎ የነበረው የንግድ ልውውጥ፣ የሌለ ያህል የቀነሰ ሲሆን፣ አካባቢውም ከፍተኛ ወታደራዊ ቀጠና ሆኗል፡፡

ሰላም ታደሰ ደምሴ፣ መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገው፣ የአንድ የደህንነት ምርምር ተቋም ተማራማሪ ናቸው፡፡ የሰላም ሥምምነቱ ፍሬ ፣ አሁንም ገና ተግባራዊ አለመደረጉን ይገልጻሉ፡፡ ለዚህም ደግሞ አንደኛው ምክንያት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው የትግራይ ክልል ዘንድ፣ ኤርትራን አስመልክቶ ያለውን የቆየ ጥርጣሬ ሊያስወግድ አለመቻሉ ነው ይላሉ፡፡ ሁለቱ አገሮች፣ ሁለት አስርት ዓመታት ፈጅቷል፣ ከተባለው ውዝግብ ውስጥ ከመግባታቸው በፊት፣ እኤእ ከ1998 እስከ 2000 ድረስ፣ ኤርትራና ኢትዮጵያ፣ የ80ሺ ሰዎች ህይወት ፈጅቷል የተባለውን የድንበር ጦርነት ተዋግተዋል፡፡ የአሁኑን የሰላም ሥምምነቱ አስመልክቶ ሰላም ደምሴ እንዲህ ይላሉ

“ከዚህ የሰላም ሥምምነት ብዙ እንጠብቃለን፡፤ ከጊዜ አንጻር ብናየው ከሁለት ዓመታት በላይ ሆኖታል፡፡ ስለሆነም አሁን ከሰላሙ ሥምምነት ብዙ ፍሬዎችን ማየት ነበረብን፡፡ መሬት ላይ ያለው ግ ን ፍጹም የተለየና የዚህ ተቃራኒ ነው፡፡”

በሁለቱ ሃገሮች ድንበር አካባቢ ባሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ፣ ያለው ግንኙነት በጣም ውስን መሆኑን፣ ሰላም ይናገራሉ፡፡ አንደኛው የመገናኛ መስመር፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ፌደራል ወታደሮች፣ ሰፍረው እንዲቆዩ በተደረገበት፣ አዋሳኝ በሆነው የኤርትራ ድንበር አካባቢ ነው፡፡ ሥምምነቱ እንደተካሄደ ፣ የንግድድ ልውውጡን ለማካሄድ፣ አራት የድንበር ኬላዎች እንዲከፈቱ ቢደረጉም፣ በትግራይ ክልል በኩል ጥያቄዎች በመነሳታቸው፣ ኬላዎቹ የተዘጉት ወዲያው ነበር፡፡

አወዛጋቢዎቹን የድንበሩ አካባቢም ለመከለል፣ የሚደረገው ጥረትም፣ ወዴትም አልተመራደም፡፡ በተለይም በሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ የምትገኘውን፣ የባድመን ከተማ አካባቢ ወደ ኤርትራ እንዲከለል፣ እኤአ በ2002 በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ኮሚሽን የተላለፈው ውሳኔ፣ ተግባራዊ አልተደረገም፡፡ በዚህ የተነሳ በአካባቢው እቅንስቃሴ ማድረግ የተገደበ ነው፡፡ ሰላም እንዲህ ብለዋል

“በኤርትራ በኩል ድንበር አቋርጦ ሲወጣ የተገኘ ሰው በጥይት ይመታል የሚለው ህግ አሁንም ይሰራል፡፡ በትግራይም በኩል ያለው ድንበር አሁንም በወታደሮች እንደተጠበቀ ነው፡፡”

ሁለቱም መንግሥታት ስለ ሥምምነቱ የሰጡት አስተያየት የለም፡፡

ማርቲን ፕላውት በለንደን ዩኒቨርስቲ ሲነየር ተማራማሪ ናቸው፡፡ እሳቸው እንደሚሉት፣ ኢትዮጵያን ወደ ሶሶት አስርት ዓመታት ለተጠጋ ጊዜ ሲያስተዳደራት የቆየውና፣ በአዲስ አበባው የፌደራል መንግሥት ተወግዶ ፣ በትግራይ ክልል የሚገኘው አስተዳደር፣ በአዲስ አመራር ካልተተካ በቀር፣ የሰላም ሥምምነቱን ተግባራዊ ማድረግ ይቸግራል፡፡ ክልሉም ከፌዴራል መንግሥት ጋር ውዝግብ ውስጥ የገባ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት በሃገሪቱ መንግሥት ህገወጥ ነው የተባለውን ምርጫ ማካሄዱን ገልጸዋል፡፡ ማርቲን ፕላውት፣ አክለውም የሚከተለውን ተናግረዋል

“በትግራዋይና በኤርትራውያን በመካከል ያለውና እንዲሁም በመሪዎቻቸውና በነሱ መካከል ያለው ግንኙነት በጣም መጥፎ ነው፡፡ በትግራይ አዲስ ፓርቲ ወደ ሥልጣን ካልመጣ በስተቀተር ምንም የሚሻሻል ነገር አይኖርም፡፡ ችግርሩ ወደ ኋላ ከ1970ዎቹ ጀምሮ የነበረ ነው፡፡ በጣም ሥር የሰደደና እጅግ የመረረ የግል ጠብ ሳይቀር ያለበት ነው፡፡ በእኔ እምነት እንዚህ ችግሮች ተመልሰው የሚጠገኑ አይመስለኝም፡፡”

ማርቲን ጨምረው እንደገለጹት፣ ከሰላም ስምምነቱ በስተጀርባ በተጠቀሱት ድንበሮቹ አካባቢ ያለው ፖታሲየም የሚባለው ማዕድን ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ገና በምድር ያለ ማአድን፣ ክምቹትም ከፍተኛ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ደናኪሊ የሚባል አንድ የአውስትራልያ ኩባንያ እየተሳፈተበት መሆኑን ይናገራሉ፡፡

“እጅግ ትልቅ፣ በጣም ትልቅ የሆነ የፖታሽ ማእድን መጠባበቂያ ክምችት አለ፡፡ ለዓለምቀፍ ገበያ ምናልባትም ለ200 ዓመታት ያህል ሊውል ይችላል፡፡ ከዚሁ ሁሉ ነገር በስተጀርባ ያለው እሱ ነው፣ ሰዎች ግን ስለዚህ ነገር በፍጹም አያወሩም፡፡”

የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች በመጨረሻ የተገናኙት ባለፈው ሐምሌ ወር ነው፡፡ በወቅቱ ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አህመድ፣ ኤርትራን የጎበኙ ሲሆን፣ ለረጅም ጊዜ ሲተች የቆየውንና በግዴታ የሚካሄደውን የብሄራዊ ወታደሮች ሥልጠና የምርቃት ፕሮግራም ላይ ተገኝተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

የኢትዮ ኤርትራ የሰላም ሥምምነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:01 0:00


XS
SM
MD
LG