በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደኢትዮጵያ በቀን ከስምንት መቶ በላይ የደቡብ ሱዳን ስደተኛ እየገባ ነው


የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ
የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ

አኮቦ ወንዝ ላይ - ስደት በጀልባ ወደ ኢትዮጵያ
አኮቦ ወንዝ ላይ - ስደት በጀልባ ወደ ኢትዮጵያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:07 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኢትዮጵያ የደቡብ ሰዳን ግጭት ከተጀመረ ካለፈው ታኅሣስ ወዲህ ባለፈው ጊዜ ውስፋ 130 ሺህ ደቡብ ሱዳናዊያን ስደተኞችን መቀበሏንና እስከ ያዝነው የአውሮፓ ዓመት መጨረሻ በሚቀሩት ሰባት ወራት ውስጥ ይህ ቁጥር እስከ 350 ሺህ ሊደርስ ይችላል ብሎ እንደሚጠብቅ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ የሚገኙት የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር - የዩኤንኤችሲአር የኢትዮጵያ ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ክሱት ገብረእግዚአብሔር ለቪኦኤ በሰጡት ቃል በአሁኑ ጊዜ በቀን ከ800 እስከ 1000 ስደተኛ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ - ኩሌ መጠለያ
የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ - ኩሌ መጠለያ
ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም ድንበሮቿ አቅራቢያ ባሉ የስደተኞች መጠለያዎች ውስጥ ከ550 ሺህ በላይ ከሶማሊያ፣ ከኤርትራ፣ ከሱዳንና ከኬንያ የገቡ ስደተኞች መኖራቸውን አቶ ክሱት አመልክተው ከግማሽ የሚበልጡት ግን የሶማሊያ ስደተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ጋምቤላ ውስጥ በሦስት የመግቢያ ኬላዎች እየተሻገሩ እየገቡ ያሉት ደቡብ ሱዳናዊያን በአምስት የስደተኞች ሠፈሮች ከመግባታቸው በፊት የጤና ምርመራ እንደሚደረግላቸውና በቅርቡ ደቡብ ሱዳን ውስጥ መቀስቀሱ በተነገረው የኮሌራ ሥጋት ምክንያት የኮሌራ ዝግጁነት ዕቅድ ወጥቶ በጥንቃቄ እየተሠራ መሆኑን አቶ ክሱት ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪና ዝርዝር መረጃ የተያያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG