ባላንታየር —
የማላዊ መንግሥት መንገድ ላይ የሚለምኑና ልጆቻቸው በልመና የተሠማሩ ወላጆች እንዲያዙ አዝዟል። “አብዛኞቹ በየመንገዱ ለልመና የተሠማሩ ሰዎች እንደገቢ ምንጭ ይዘውት እንጂ ኑሮ አስገድዷቸው አይደለም” ይላል መንግሥቱ።
ፖሊስ የታዘዘውን እርምጃ መውሰድ አልጀመረም፡፡ ትዕዛዙ ግን የሕዝብ ትችቶችን አስከትሏል። ከባላንታየር የደረሰን የሪፖርተራችን የላሜክ መሲና ዘገባ አለ፤ ትዝታ በላቸው ታቀርበዋለች።