No media source currently available
የማላዊ መንግሥት መንገድ ላይ የሚለምኑና ልጆቻቸው በልመና የተሠማሩ ወላጆች እንዲያዙ አዝዟል። “አብዛኞቹ በየመንገዱ ለልመና የተሠማሩ ሰዎች እንደገቢ ምንጭ ይዘውት እንጂ ኑሮ አስገድዷቸው አይደለም” ይላል መንግሥቱ። ፖሊስ የታዘዘውን እርምጃ መውሰድ አልጀመረም፡፡ ትዕዛዙ ግን የሕዝብ ትችቶችን አስከትሏል።