በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማላዊ ውስጥ 232 ኢትዮጵያዊያን ታስረዋል


ማላዊ
ማላዊ

ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ድንበር አቋርጣችኋል የተባሉ ኢትዮጵያዊያን ማላዊ ውስጥ በእሥር ላይ ይገኛሉ።

ሊሎንግዌ - የማላዊ ዋና ከተማ
ሊሎንግዌ - የማላዊ ዋና ከተማ

please wait

No media source currently available

0:00 0:10:28 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ድንበር አቋርጣችኋል የተባሉ ኢትዮጵያዊያን ማላዊ ውስጥ በእሥር ላይ ይገኛሉ።

እነዚህ 232 ኢትዮጵያዊያን የሚገኙበት ሁኔታም እጅግ አስከፊና ጤንነትንም የሚጎዳ መሆኑን እዚያው ኗሪ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ከእነዚህም አንዷ ዋና ከተማይቱ ሊሎንግዌ ውስጥ ከሃያ ዓመታት በላይ የኖሩት ወ/ሮ ዮዲት በላቸው ናቸው።

ሊሎንግዌ በሚገኘው ማዉላ ወኅኒ ታስረው የሚገኙት ኢትዮጵያዊያን ለእሥር የተዳረጉት ሥራ ፍለጋ በሚል በማላዊ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመሻገር ሲሞክሩ «ከህግ ውጭ ድንበር ለመሻገር ሞክራችኋል» ተብለው መሆኑንም ወ/ሮ ዮዲት ገልፀል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎቹን ለማስለቀቅ ምን እያደረገ ነው? ማላዊ ውስጥ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የለም። የዚያን አካባቢ ጉዳይ የሚከታተለው ናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስለሆነ የኤምበሲው ሁለተኛ ተቀዳሚ ፀሐፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጉ በርኸን አነጋግረናል።

አቶ አንዳርጉ እንዳሉት ጉዳዩ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደርሶ ክትትል እየተደረገበት ነው።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG