በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በማላዊ እስር ቤቶች


የማላዊ ካርታ
የማላዊ ካርታ

ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመዝለቅ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ማላዊ የገቡ ናቸው የተባሉ ኢትዮጵያውያን፣ በተለያዩ የማላዊ እስር ቤቶች ይገኛሉ። ይሁንና የቅጣት ጊዜያቸውን ጨርሰው ነገር ግን ከእስር ያልተፈቱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በርካታ ነው።

ማላዊ ውስጥ በልዩ ልዩ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ወዳገራቸው ለመመለስ እርዳታ እየጠየቀ መሆኑን፣ እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው ዓለማቀፍ የፍልሰተኞች ማኅበር (USAIM) ሰሞኑን ባሰራጨው በራሪ ወረቀት የድረሱልን ጥሪ አቅርቧል።

ከዚህ ቀደም ባቀረብንው ዝግጅት ማላዊ የሚገኘውን የዓለማቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ቢሮ ኃላፊ ጠይቀን እንደተረዳንው፣ በገንዘብ ምክንያት ያለው ችግር እንደማያሳስብ ኃላፊው ገልጸው ነበር። ማለትም ድርጅታቸው ወጪውን እንደሚሸፍን። በአሁነ ወቅት እየተጠየቀ ያለው ግን፣ ለመጓጓዣቸው የሚሆን በነፍስ-ወከፍ ቢያንስ $500.00 ያስፈልጋል። ይህም ማለት $500.00 ከስደተኞቹ እየጠየቁ ነው።

የአሜሪካ ድምፅ “የትራንስፖርት ወጪያቸውን እንሸፍናለን ብለውኝ አልነበር ወይ?” ብለን ጠይቀናል። ነገር ግን፣ ማላዊ የሚገኙት የዓለማቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ኃላፊ ለጊዜው በስልክ አልተገኙም። ይሁንና ወደ ፕሪቶሪያ ደውውለን አቶ ይጥና ጌታቸውን አግኝተናቸዋል። አቶ ይጥና፣ ማላዊን ጨምሮ የደቡባዊ አፍሪቃን ክልል የሚመለከት በአከባቢው ቢሮ የዓለማቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM Regional Office) ውስጥ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለማስቀረት የሚሰሩ ባለ ሞያ ናቸው።

ከዚህ ቀደም የተገባው ቃል ምን ሆነና ነው አሁን ይህ የገንዘብ ጥያቄ የተነሳው አቶ ይጥና? ብለን ጠየቅን።

“የማላዊው የዓለማቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ዋና ኃላፊ ግን በወቅቱ ስንወያይ፣ ለጉዞ የሚሆን ወጪ ችግር እንደሌለ” ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንግሥት ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። መንግሥት ደግሞ ለዜጎቹ ግድ አለውና፣ ኢትዮጵያውያኑ በገንዘብ እጥረት የተነሳ ባዕድ አገር ሲቀሩ ዝም ስለማይል፣ ከጉዳዩ ጋር ቀረቤታም ስላላቸውና፣ ከዚህ ቀደምም ጥሩ ትብብር ስላደረጉልን፣ ወደ ናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምበሲ ደውለን 1ኛ ጸሓፊውን አቶ አንዳርጉ በርኸን አገኘን።

በሚቀጥለው ሳምንት በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ዘገባ እንደሚኖረን እንገልጻለን፣ አዲሱ አበበ ጉዳዩን በዝርዝር ያቀረበበት ዘገባ አለ። ይህን ዘገባ ከዚ በታች የተያያዘውን የድምፅ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።

ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በማላዊ እስር ቤቶች /ርዝመት -11ደ27ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:27 0:00

XS
SM
MD
LG