በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ከማላዊ ሊመለሱ ነው ተባለ


በተለያዩ የማላዊ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በቅርቡ ወዳገራቸው እንደሚጓጓዙ፣ IOM-ዓለማቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅትና ማላዊ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለቪኦኤ ገለጹ። ይህ የተገለጸው ዋና ጽ/ቤታቸው ኬንያ-ናይሮቢ የሆነውና ማላዊንም የሚያካትቱት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በትናንቱ ዕለት ማላዊ ተገኝተው እዚያ ለሚገኙ የIOM, የMSF-ድንበር-የለሽ የሐኪሞች ድርጅትና የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት ባረረጋገጡበት ወቅት ነው።

በልዩ ልዩ እስር ቤቶች የሚገኙትና ወደ 279 የሚሆኑት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ወዳገራቸው የሚጓጓዙት፣ በአንድ ጊዜ መሆኑንም አምባሳደሩ መናገራቸውን፣ ከማላዊ ያገኘንው መረጃ አመልክቷል።

ስቲቨንስ ቶርሺዬ፣ ማላዊ የሚገኘው የIOM-የዓለማቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ኃላፊ ናቸው። በትናንቱ ዕለት ማላዊ ውስጥ ከአምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጋር በተገናኙበት ወቅት ፍልሰተኞቹን በተመለከተ የተካሄደውን ሁኔታ ሲገልጹ፣ “በቅርቡ አውሮፕላን ልከው እንደሚያጓጉዟቸው፣ የጉዞ ሰነድ ለሌላቸውም እንደሚዘጋጅላቸው ገልጸውልናል። ይህ ሁሉ በቀጣዮቹ ቀናት ሁሉም ፍልሰተኞች በሰላም ወዳገራቸው እንደሚሄዱ ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።

ፍልሰተኞቹ ወዳገራቸው እንደሚጓጓዙ ይፋ የተደረገውን ዜና ከMSF-ድንበር የለሽ የሐኪሞች ድርጅት የማላዊ ምክት ኃላፊ ከሚስ ኒኮሌት ጃክሰለንም የስልክ መልዕክት ተረድተናል።

በአሁኑ ወቅት ስንት ፍልሰተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚጓጓዙና ሁላቸውም ባንድ ጊዜ ስለመሄዳቸው፣ ሚስተር ስቴፈንስከ ተጠይቀው እንድህ ብለዋል።

“በግምት ለመናገር፣ በቅርቡ የተደባለቁትን 56«ኡን» ጨምሮ ወደ 279 ይሆናሉ። አምባሳደሩ እንደገልጹልን ከሆነም፣ አዎ ሁሉም ባንድ ጊዜ ነው በቅርቡ የሚጓጓዙት።”

በዚህ ዘገባ፣ ሁሉም ባይሆኑም፣ አንዳንዶቹ ማላዊ የሚገኙ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ተጠቅሰዋል። እኛ ደግሞ ይህን ማላዊ ታስረው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ዘገባ ስንሰራ፣ ከጅምሩ፣ ምንጫችን፣ አንዷ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አባል፣ ወ/ዮዲት በላቸው ነበሩ። ትናንት ከአባሳደር ዲና ሙፍቲ ጋር የተካሄደውን ውይይትና ስለ ፍልሰተኞቹም የተናገሩትን በሙሉ ገልጸውልናል።

ሙሉ ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ከማላዊ ሊመለሱ ነው ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:59 0:00

XS
SM
MD
LG