በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቦኮ ሀራም አማጽያን ከተጠለፉት 219 የሰሜን-ምሥራቅ ቺቦክ ልጃገረዶች አንዷ በህይወት ተለቀቀች


ፋይል ፎቶ - በቦኮ ሀራም አማጽያን ከተጠለፉት 219 የሰሜን-ምሥራቅ ቺቦክ ልጃገረዶች እ.አ.አ. 2014/ከቦኮ ሀራም ቪድዮ የተገኘ/
ፋይል ፎቶ - በቦኮ ሀራም አማጽያን ከተጠለፉት 219 የሰሜን-ምሥራቅ ቺቦክ ልጃገረዶች እ.አ.አ. 2014/ከቦኮ ሀራም ቪድዮ የተገኘ/

የተገኘችዋ ልጅ ስም አሚና አሊ ይባላል። በጅምላ ከታፈኑትና ከተወሰዱት ልጃገረዶች መሃል ይቺኛዋ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘች መሆንዋ ነው።

ከሁለት ዓመት በፊት በናይጄሪያው ነውጠኛ በድን ቦኮ ሀራም አማጽያን ከተጠለፉት 219 የሰሜን-ምሥራቅ ቺቦክ ልጃገረዶች መካከል አንዷን እንዳስለቀቀ፣ የናይጄሪያው ጦር ዛሬ ረቡዕ አስታወቀ።

በጅምላ ከታፈኑትና ከተወሰዱት ልጃገረዶች መሃል ይቺኛዋ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘች መሆንዋ ነው።

የጦር ኃይሉ ቃል-አቀባይ ሳኒ ኡስማን በቴክስት መልዕክቱ እንዳሰፈረው፣ ልጃገረዲቱ የተገኘችው፣ በሰሜን-ምሥራቅ ናይጄሪያዋ ዳምቦዋ ከተማ፣ ባሌ በተሰኘ መንደር ውስጥ ነው።

አቦኩ ጋጂ የተሰኘ አንድ የቺቦክ የአካባቢው ደኅንነት ጠባቂ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጠው ቃል መሠረት፣ ጸጥታ አስከባሪዎቹ ልጃገረዲቱን ያገኟት፣ ቦኮ ሀራም ምሽግ አካባቢ ደፈጣ ይዘው በነበረበት ወቅት ነው። ጋጂ እንደገለጸው፣ የተገኘችዋ ልጅ ስም አሚና አሊ ይባላል።

XS
SM
MD
LG