በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካሜሩን ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች በቦኮ ሀራም ላይ የጋራ አቋም መያዛቸው ተሰማ


የካሜሩን ካርታ
የካሜሩን ካርታ

ሙስሊሞቹ ጸሎት ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ክርስቶያኖች መስጊዶችን ይጠብቃሉ፣ ክርስቲያኖቹ ጸሎት ላይ ሲሆኑ ደግሞ ሙስሊሞቹ አብያተ-ክርስቲያናትን ከጥቃት ይከላከላሉ።

የካሜሩን ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች በቦኮ ሀራም ላይ የጋር አቋም መያዛቸው ተሰማ።

በዚሁ መሠረት፣ ሙስሊሞቹ ጸሎት ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ክርስቶያኖች መስጊዶችን ይጠብቃሉ፣ ክርስቲያኖቹ ጸሎት ላይ ሲሆኑ ደግሞ ሙስሊሞቹ አብያተ-ክርስቲያናትን ከጥቃት ይከላከላሉ። በተለይ የሁለቱ ቤተ-እምነቶች ትብብር የጀመረው፣ ቦኮ ሀራም በአምስት መስጊዶች ላይ ጥቃት ካካሄደ በኋላ ሲሆን፣ ሁለቱም ቦኮ ሀራምን በጋራ ጠላትነት መፈረጃተው ታውቋል።

በማለዳ ጸሎት የበሚተላለፈው መልዕክት፣ በካሜሩን ከናይጄሪያ ጋር በምትዋሰንበት ሞዞጎ (Mozogo) በተባለ ስፍራ ለሚገኝ አንድ ማከላዊ መስጊድ አማንያን ቀጣይ ጥሪ ያቀርባሉ። አማንያኑ ጸሎት ሲጠመዱ፣ ለስፍራው የተመደቡ ጠባቂዎች ደግሞ፣ ማንም ፀጉረ-ልውጥ ወደ መስጊዱ እንዳይጠጋ ይጠባበቃሉ። ከነዚህ መካከል አንዱ፣ የ55 ዓመቱ የካሜሩን ሉተራን ወንጌላዊ ቤተ-ክርስቲያን አገልጋይ ጃኪስ ማባሊ (Jacques Mabali) ናቸው።

"ሙስሊሞቹ ለጸሎት ሲሰበሰቡ መስጊዳቸው ላይ ጥቃት እንዳይደርስ ጥበቃ ለማካሄድ ከቤተ-ክርስቲያኔ የበላይ መሪዎች ትዕዛዝ ተሰጥቶኝ ነው እዚህ ያለሁት" ብለዋል። "ለአገሬ ደኅንነት ማኅበራዊ አገልግሎት እየሰጠን ነው" ያሉት ወንጌላዊው የሉተራን ቤተ-ክርስቲያን አገልጋይ ጃኪስ ማባሊ፣ "እንደ ክርስቲያንም አገሬንም ሆነ ሕዝባችንን ከአደጋ የመከላከል ኃላፊነት አለብኝ" በማለት አክለዋል።

ኢብራሂም ሙክታር፣ በሞዞጎ (Mozogo) መስጊድ አባል የሆነ ወጣት ሙስሊም ነው። "የአገሬ ዜጎች የሆኑ ክርስቶያኖች በነውጠኛው ቡድን እየተከበቡና ጥቃት እየደረሰባቸው ስለሆነ፣ ያን እየተከላከልን ነው" ብሏል።

በማከልም፣ "ካሜሩን ያለን ሙስሊሞችና ክርስቶያኖች፣ ወንድማማችና እትማማቾች ነን። ስለዚህም ነው ቦኮ ሀራም አብያተ-ክርስቲያናት ላይ ጥቃት እንዳያደርስ የምከላከለው" ብሏል።

አንዳንድ የቤተሰቡ አባላት ክርስቲያኖች መሆናቸውንም የገለጠው ኢብራሂም፣ "ሁለታችንም ግን ሽብርተኛነትን ለመዋጋት የጋራ ትብብር ፈጥረናል" ብሏል።

የናይጄሪያው ሽብርተኛ ቡድን ቦኮ ሀራም፣ ካሜሩን ውስጥ በሙሉ ኃይል መንቀሳቀስና ግድያ፣ ዝርፊያ፣ እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን፣ አብያተ-ክርስቲያናትን፣ መስጊዶችንና ገበያዎችንና ማቃጠል ከጀመረ 3ኛ ዓመቱን ይዟል። ከሁለቱም ቤተ-እምነቶች የተውጣጣው ጠባቂ ኰሚቴ ሊቋቋም የቻለው፣ ቦኮ ሀራም በተለይም ሴቶች አጥፍቶ ጠፊዎችን ካለፈው ዓመት መግቢያ ገደማ ወዲህ ማሰማራት ከጀመረ በኋላ ለመንግሥቱ እገዛ ለመስጠት እንደሆነ ታውቋል። ለምሳሌ፣ ካሜሩን ላይ ጥቃት የሚያካሂደው በዚያች አገር እስላማዊ መንግሥት ለማቋቋም መሆኑን የሚገልጸው ቦኮ ሀራም፣ ባለፈው ወር ተጠርጣሪዎቹ በመስጊዶች ላይ ጥቃት ማካሄዳቸው አይዘነጋም።

የሰሜናዊ ካሜሩን ገዢ ሚድ-ጂ-ያዋ(Midjiyawa) ባካሪ (Bakari) ካሜሩንን ከጋራ ጠላት ለመከላከል፣ ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች በአንድነት በመቆማቸው "እንኳን ደስያላች" የሚል ማበረታቻ መልዕክት አስተላልፈው፣ ሌሎችም ተመሳሳይ አቋም እንዲይዙ ጥሪ አቅርበዋል።

ከካሜሩን 23.7 ሚልዮን (million) ሕዝብ 40% ክርስቲያኖች፣ 20% ደግሞ ሙስሊሞች ሲሆኑ የተቀሩት፣ አገር-በቀል እምነት ተከታዮች ናቸው።

ከያውንዴ (Yaounde)የቪኦኤ ዘጋቢ ሞኪ ኤድዊን ኪንድዜካ (moki edwin kindzeka) ሪፖርት ልኮልናል፣ አዲሱ አበበ አጠናቅሮ አቅርቦታል። ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

የካሜሩን ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች በቦኮ ሀራም ላይ የጋራ አቋም መያዛቸው ተሰማ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:36 0:00

XS
SM
MD
LG