በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አይስስ የ30 ዓመቷ ጋዜጠኛ ሩቅያ ሃሰንን ሦርያ ውስጥ ገደለ


የ30 ዓመቷ ጋዜጠኛ ሩቅያ ሃሰን (Ruqia Hassan) ከማኅበራዊ ሚድያ የተገኘ ፎቶ
የ30 ዓመቷ ጋዜጠኛ ሩቅያ ሃሰን (Ruqia Hassan) ከማኅበራዊ ሚድያ የተገኘ ፎቶ

ሰለባዋ፣ በአይስስ(ISIS) ቁጥጥር ስር ከሚገኝ ክልል በራቃ (Raqqa)ሆና ነበር በነፃ ጋዜጠኛነት ትዘግብ የነበረችው።

ሦርያ ውስጥ የሚገኙ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንዳስታወቁት፣ እራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚታወቀው ነውጠኛ ቡድን፣ ለመጀመራ ጊዜ አንዲት ሴት ጋዜጠኛን ገደለ። ሰለባዋ፣ በአይስስ(ISIS) ቁጥጥር ስር ከሚገኝ ክልል ሆና ነበር በነፃ ጋዜጠኛነት ትዘግብ የነበረችው።

የ30 ዓመቷ ሩቅያ ሃሰን (Ruqia Hassan) ሦርያ ውስጥ አይስስ(ISIS)በሚቆጣጠረው በራቃ (Raqqa) ያለው ሕይወት ምን እንደሚመስል ነበር በየዕለቱ የምትዘግበው። ያ ክልል፣ አንዳንዴም፣ ለአይስስ(ISIS)የሚሰነዘር የአየር ጥቃት ይወርድበት እንደነበር ታውቋል።

ሩቅያ ሀሰን አንዳንዴም፣ ኒሳን ኢብራሂም (Nissan Ibrahim) በሚል የፌስ ቡክ ስም(Facebook) ትታወቅ ነበር።

ጋዜተኛዋ የተገደለቸበት ቀን በትክክል አይታወቅም። ሆኖም፣ ሰሞኑን በተጠናቀቀው ያአውሮፓውያኑ 2015 ከማኅበራዊ ድረ-ገጽ ላይ ጠፍታ እንደነበር ነው የተገለጸው።

በእርግጥ መሞቷ የተረጋጠው ደግሞ በዚህ ሳምንት ውስጥ ነው። የዜና ዘገባውን ከድምጽ ፋይልይ ያገኙታል።

አይስስ የ30 ዓመቷ ጋዜተኛ ሩቅያ ሃሰንን ገደለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:05 0:00

XS
SM
MD
LG