በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናትድ ስቴትስ ጦር ሠራዊት ጂሃዲ ጆን ላይ ያነጣጠረ ያየር ድብደባ አካሄደ

ጂሃዲ ጆን (Jihadi John)በበርካታ ቪዲዮኦውች ላይ የምዕራባውያን ታጋዮችን አንገት ሲቀላ ታይቷል
ጂሃዲ ጆን (Jihadi John)በበርካታ ቪዲዮኦውች ላይ የምዕራባውያን ታጋዮችን አንገት ሲቀላ ታይቷል

ምዕራባውያን የስለላ ድርጅቶች መሃመድ ኤምዋዚ (Mohammed Emwazi) መሆኑን የሚገልጹት ነውጠኛ፣ በትላንት ማታው ራቃ ሶርያ (Raqqa, Syria) ውስጥ በተካሄደ የድሮን ጥቃት ስለመገደሉ ግን፣ ባለሥልጣናት ወድያውኑ የሰጡት ማረጋገጫ የለም።

የዩናትድ ስቴትስ ጦር ሠራዊት ጂሃዲ ጆን (Jihadi John) እየተባለ በሚጠራው አደገኛ እንግሊዛዊ የእስላማዊ መንግሥት ሚሊሽያ ላይ ያነጣጠረ ያየር ድብደባ ማካሄዱን አስታወቀ።

ጂሃዲ ጆን (Jihadi John)በበርካታ ቪዲዮዎች ላይ የምዕራባውያን ታጋዮችን አንገት ሲቀላ ታይቷል።

ምዕራባውያን የስለላ ድርጅቶች መሃመድ ኤምዋዚ (Mohammed Emwazi) መሆኑን የሚገልጹት ነውጠኛ፣ በትላንት ማታው ራቃ ሶርያ (Raqqa, Syria) ውስጥ በተካሄደ የድሮን ጥቃት ስለመገደሉ ግን፣ ባለሥልጣናት ወድያውኑ የሰጡት ማረጋገጫ የለም።

ማንነታቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ከፍተኛ የዩናትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ለበርካታ ብዙሃን እንደተናገሩት ግን መሃመድ ኤምዋዚ (Mohammed Emwazi) የነበረበት ተሽከርካሪ በትክክል የተመታ በመሆኑ ሳይሞት አልቀረም ብለዋል። ዜናውን ከዚህ በታች ካለው ፋይል ያድምጡ።

የዩናትድ ስቴትስ ጦር ሠራዊት ጂሃዲ ጆን (Jihadi John) ላይ ያነጣጠረ ያየር ድብደባ አካሄደ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:43 0:00

XS
SM
MD
LG