በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጆን ኬሪ አይስልን (ISIL)ለመዋጋት ሁነኛ የጥምረት ግንባር ተደራጅቷል ብለዋል


የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚስተር ጆን ኬሪ ( John Kerry)
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚስተር ጆን ኬሪ ( John Kerry)

ጽንፈኛውን እስላማዊ ቡድን ISIL’ን ለመዋጋት ሁነኛ የጥምረት ግንባር ተደራጅቷል፤ ቡድኑ እንደኢደመሰስም “ጽኑ እምነት አለኝ፤” ሲሉ የዩይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንትር ጆን ኬሪ (John Kerry) ተናገሩ።

በአረብ ኢሜሬት በሥራ ጉብኝት ላይ የሚገኙት ጆን ኬሪ ከCBS የቴሌቭዥን ጣቢያ Today Show ከተባለው ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በሰጡት አስተያየት ይህን ግብ እውን ለማድረግ የሚያስችል ሁነኛ እቅድ መኖሩን አመልተው፤ በቡድኑ ይዞታዎች ላይ ሕብረ ብሔራዊው ጥምረት ኃይል የሚያካሂደውን የዓየር ድብደባ የምትመራው አገራቸው ወታደራዊ፥ የጸረ-ሽብርና የዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን በሙሉ እያጠናከረች መሆኗን ተናግረዋል።

በፈረንሳይ፥ በባኖስና በግብጽ የደረሱትን የሽብር ጥቃቶች የፈጸሙት አሸባሪዎች የጽንፈኛው ቡድን ጀሌዎች በሶሪያና በኢራቅ በሚያደርጉት ተነሳስተው መሆኑን የጠቆሙት Kerry የጥምረቱ ኃይል በሁለቱ አገሮች የሚያካሂደውን ዘመቻ በመጪው ቀናት ውስጥ ይበልጥ አጠናቅሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚንትሩ አክለውም፤ የዩይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ፤ ISIL’ን ለመደምሰስ የሚያግዙ አዳዲስ ሃሳቦችን እንዲያቀርቡ የአስተዳደራቸው ባለሥልጣናት መጠየቃቸውን ገልጠዋል። የዜና ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

ጆን ኬሪ አይስልን ( ISIL)ለመዋጋት ሁነኛ የጥምረት ግንባር ተደራጅቷል ብለዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:23 0:00

XS
SM
MD
LG