በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የብሪታንያ የጦር አይሮፕላኖች በሶርያ የአየር ድብደባ ጀመሩ


የብሪታንያ የሮያል አየር ሃይል ቶርኔዶ ተዋጊ ጀት የጦር አይሮፕላን
የብሪታንያ የሮያል አየር ሃይል ቶርኔዶ ተዋጊ ጀት የጦር አይሮፕላን

የብሪታንያ የጦር አይሮፕላኖች ሶርያ ውስጥ የአየር ድብደባ ጀምረዋል። ድብደባውን የጀመሩት የብሪታንያ የምክር ቤት አባላት እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለውን ጽንፈኛ ቡድን ለማሸነፍ እንዲቻል የሀገሪቱ ስትራተጂ እንዲሰፋ ዴቪድ ካምሩን ያቀረቡትን ሃሳብ ካጸደቀ በኋላ ነው።

የሮያል አየር ሃይል ቶርኔዶ ተዋጊ ጄት አይሮፕላኖች ቆጵሮስ ከሚገኘው የብሪታንያ የአየር ሰፈር ተንስተው ሶርይ ያሉትን ኢላማዎች ከመቱ በኋላ በሰላም ወደ ሰፈራቸው እንድተመለሱ የብሪታንያ የመከላከያ ባለስጣኖች ዛሬ ተናግረዋል።

የአየር ድብደባው ኢላማ ያደረገው እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለው ጽንፈኛ ቡድን የሚቆጣጠራቸው የነዳጅ ዘይት መስኮችን እንደሆነ የብሪታንያ የመከላከያ ሚኒስቴር በትዊተር ገልጿል። ስለድብደባው ውጤት ግን የተናገረው ነገር የለም።

በዩናትድ ስቴትስ (United States) የሚመራው ጥምረት ተዋጊ አይሮፕላኖች ደግሞ ሶርያ ውስጥ በእስላማዊው ጽንፈኛ ቡድን ኢላማ ላይ 14 ድብደባዎች አካሂደዋል። ኢራቅ ውስጥም 18 የአየር ድብደባዎች አካሂደዋል። ዋናው ኢላማ የጽንፈኛው ቡድን የነዳጅ ዘይት ሃብት እንደሆነ ዛሬ የወጣ የጥምረቱ መግለጫ ጠቁሟል። የዜና ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የብሪታንያ የጦር አይሮፕላኖች በሶርያ የአየር ድብደባ ጀመሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:21 0:00

XS
SM
MD
LG