በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን አከባበር በዓለም ዙርያ


በሴቶች ጉዳዮች በኩል የታዩ መሻሻሎች የሚንጸባረቁበት፣ አስፋላጊ ለውጦች እንዲደረጉ ጥሪ የሚቀርብበት፣ በዓለም ደረጃ ለጾታ እኩልነት ለሚሰሩ ሴቶች ብርታትና ቁርጠኝነት እውቅና የሚሰጥበት እለት ነው።

ዛሬ እ.አ.አ. አቆጣጠር ማርች ስምንት ማለት መጋቢት ስምንት በዓለምአቀፍ ደረጃ የሚከበር የሴቶች ቀን ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እ.አ.አ. በ 1975 ዓ.ም. ዕለቱን የሴቶች መብትና የዓለምአቀፍ ሰላም የሚታሰብበት እንዲሆን ሰየመው። በ 1977 ዓ.ም. ደግሞ በመንግስታቱ ድርጅት በውሳኔነት ጸደቀ።

በሴቶች ጉዳዮች በኩል የታዩ መሻሻሎች የሚንጸባረቁበት፣ አስፋላጊ ለውጦች እንዲደረጉ ጥሪ የሚቀርብበት፣ በዓለም ደረጃ ለጾታ እኩልነት ለሚሰሩ ሴቶች ብርታትና ቁርጠኝነት እውቅና የሚሰጥበት እለት ነው።

ሴቶችና ልጃገረዶች በዓለም ደረጃ የትምህርት እድል ለማግኘት፣ እኩልነታቸው በህግ ፊት እንዲከበር፣ ሴቶች በባንክ ገንዘብ የማስቀመጥንና የማውጣትን፣ ስልጠናን የጎልማሶች ትምህርትን ለመሳሰሉት ወንዶች ለሚያገኙት መሰረታዊ አገልግሎትም ተደራሽነት እንዲኖራቸው ስለሚያደርጉት ትግል እንዲታወቅ የሚያስችልበት እለትም ነው። ሴቶች መሰረታዊ የሆነው ሰብአዊ መብታቸው እንዲከበርና የማንም ንብረት ሳይሆኑ ነጻ ስዎች ተደርገው እንዲታዩ ሲታገሉ ኖረዋል።

ሴቶችና ልጃገረዶች ካለፉት 41 ዓመታት ወዲህ በተሻለ ሁኔታ ይገኛሉ። ግን አሁንም ቢሆን ብዙ የሚቀር ነገር አለ። በዓለም ደረጃ በድህነት ከሚፈረጁት ሰዎች አብዛኞቹ ሴቶች ናቸው። በማንኛውም የዓለም ክፍል የወንዶችን ያህል መብትና እድል አለን ሊሉ የሚችሉ ሴቶች የሉም። ስራቸው ተገቢ ዋጋ አያገኝም። ከወንዶች ጋር በአንድ አይነት ስራ ላይ ተሰማርተው ወንዶች ከሚያገኙት ክፍያ በ30 እና በ40 ከመቶ ያነሰ ነው የሚከፈላቸው። በኢኮኖሚ ራሳቸውን አለመቻላቸው ራሱ በሌላውም ህይወታቸው ሃይል እንዳይኖራቸው ያደርጋል። በጾታ ላይ ለተመሰረተ ጥቃት ይጋለጣሉ።

ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን አከባበር በዓለም ዙርያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:33 0:00

እ.አ.አ. እስከ 2030 ዓ.ም. በሚኖረው ጊዜ ውስጥ (በ15 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ማለት ነው) የሴቶች እኩልነት የሚረጋገጥበት ጊዜ እንዲሆን፣ በያዝነው ዓመት ትኩረት ተሰጥቶበታል።

ይህም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ15 ዓመታት ውስጥ ዘላቂ የልማት አጀንዳ እንዲኖር ያወጣው እቅድ አካል ነው። ድርጅቱ የጾታ እኩልነትና ሰብአዊ መብት እንዲከበር እንዲሁም ሴቶች ራሳቸውን እንዲችሉ ለማደረግ ካለው ቁርጠኛነት ጋር የተያያዘ ነው።

ይህም በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውም አይነት አድልዎና ማንኛውም አይነት በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት እንዲቆም፣ ከእድሜ በታች የሆኑ ልጃገረዶችን በግዴታ መዳርና ግርዘት ማቆም የመሳሰሉትን ያካትታል። ልጃገረዶችና ወንዶች ጥራቱ የተጠበቀ የትምህርት እድል እንዲያገኙ ማድረግም በድረጅቱ ግብ ውስጥ ተካቷል።

ማንኛውም እድገት የሚፈልግ ማህበረሰብ ሴቶች ራሳቸው እንዲችሉ ከወንዶች ጋር እኩል መብት እንዲኖራቸው ለማድረግ መጀመር ይኖርበታል።

ዛሬ ተከብሮ በዋለው ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን ለሴቶችና ልጃገረዶች ክብር በመስጠት ዓለም ሴቶችና ልጃገረዶች የሚጨቆኑበት ሳይሆን መላ የብቃት መሰረታቸውን የሚተገበሩበት እንዲሆን ቆርጠን የምንነሳበት እለት ነው ሲል የዛሬው ርእሰ-አነቀጽ ሀተታውን አብቅቷል።

ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን አከባበር በዓለም ዙርያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:30 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG