በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት የቀድሞ የኡጋንዳ አማጽያን አዛዥ ጉዳይን እየሰማ ነው


ዶመኒክ ኦንግዌን (Dominic Ongwen)
ዶመኒክ ኦንግዌን (Dominic Ongwen)

ዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት ኤል አር ኤ (LRA) በሚል አሕጽሮት የሚታወቀው የጌታው ተከላካይ ሰራዊት የተባለው የኡጋንዳ አማጽያን ቡድን አዛዥ የነበረው ዶመኒክ ኦንግዌንን (Dominic Ongwen) ለፈርድ ለማቅረብ የሚያስችል በቂ ማስረጃ ይኖር እንደሆነ በሚያዳምጥበት በአሁኑ ወቅት በሰሜን ኡጋንዳ የፍትህና የሰላም ጉዳይ እያነጋጋረ ነው።

የቀድሞው የጌታው ተከላካይ ሰራዊት የተባለው የአምጽያን ቡድን አዛዥ በህግ፣ በዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት ፊት ቀርቦ ጉዳዩ ለፍርድ ለመቅረብ ይችል እንደሆነ በሚታይበት በአሁኑ ወቅት ኡጋንዳውያን በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት እየተከታተሉት ነው።

ዶመኒክ ኦንግዌን የጌታው ተከላካይ ሰራዊት በተባለው የአመጽያን ድርጅት የተጠለፈው ገና በአስር አመት እድሜው ነበር። በብዙ ሺህ ከሚቆጠሩት ልጆች ወታደሮች አንዱ ነበር ማለት ነው። ዶመኒክ ኦንግወን በርካታ ጥቃቶች በማካሄድ የሚጠበቅበትን በመፈጸም ተግባር እየተካነ በመሄዱ በጆሴፍ ኮኒ አመራር አካል ድረስ ደረሰ።

ጆሴፍ ኮኒ
ጆሴፍ ኮኒ

በመጨረሻም በያዝነው ወር እጁን በማእከላዊ አፍሪቃ ሪፑብሊክ ሰጠና ወደ ዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት ተላለፈ።

የዶመኒክ ኦግዌን ጉዳይ በመላ ኡጋንድ በቴሌቪዥን እንዲታይ ያደረገው የስደተኞች ህግ ውጥን የተባለ የሰላምና የፍትህ መርሀ-ግብሮችን የሚመራ አካል ነው። የጦርነቱ ሰለባ የሆኑት ሰዎች ከኅብረተሰቡና ከሀይማኖት መሪዎች ጋር ሆነው ጉዳዩን በቴሌቪዥን ለመከታተል ችለዋል።

የስደተኞች ህግ ውጥን ስራ አስኪያጅ ስተፈን ኦሎ ሰው የዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት ሚናን በሚመለከት ያለው አስተያየት የተለያየ እንደሆነ ገልጸዋል።

“ሰዎች አይናቸውን በቴሌቪዥን ላይ ተክለው የፍርዱን ሂደት እጅግ አጥብቀው እየተከታተሉት ነው። ጉዳዩ በቴሌቪዥን መታየት ከመጀመሩ በፊት በጦርነቱ ከተጎዱት ሰዎች ጋር ተነጋግረን ነበር። ያገኘነው ምላሽም ድብልቅ ነበር። አንዳንዶቹ በኡጋንዳ እንዲፈረድበት ነበር የፈለጉት። ሌሎች ደግሞ በዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት ቢፈረድበት የተሻለ ነው ይላሉ"ብለዋል።

ሌሎች ብዙ ኡጋንዳውያን ግን የኡጋንዳ መንግስት በጉዳዩ ላይ ለምን ጉልህ ሚና አልተጫወተም? የሚል ጥያቄ እያነሱ ነው። መንግስት ኦንግዌን በአማጽያኑ ድርጅት እንዳይጠለፍ አለመጠበቁም ራሱ አነጋጋሪ ሆኗል።

አለም አቀፍ የወንጀል ችሎቱ የጌታው ተከላካይ ሰራዊት የተባለው ድርጅት ባህሪንና ተግባራትን በሚገባ የገለጸ ቢሆንም የሀገሪቱ መንግስትና ወታደራዊው ሀይል ኦንግዌን የመሳሰሉት ልጆች በጨቅላነታቸው እንዳይጠለፉ ለመጠበቅ ያለመቻሉ ጉዳይ በችሎቱ መቅረብ ነበረበት ብለዋል ኦሎ።

ኦንግዌንን ለፍርድ ለማቅረብ በቂ ማሰረጃ ይኖር እንደሆነ የማየቱ ጉዳይ ከሶስት እስከ አምስት ቀናት ሊወስድ ይችላል። ዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት በቂ ማስረጃ አለ የሚል ከሆነ ኦንግዌን ለፍርድ ይቀርባል ማለት ነው።

ዘጋብያችን ሊዛበት ፖውላት ከካምፓላ የላከችውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቀባዋለች ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

ዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት የቀድሞ የኡጋንዳ አማጽያን አዛዥ ጉዳይን እየሰማ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:30 0:00

XS
SM
MD
LG