በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አይሲሲ በቀድሞ የኮንጎ ምክትል ፕሬዚደንት ቢምባ ላይ ብይን ሰጠ


ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (ICC) አምስ ት የተለያዩ የጦር ወንጀሎችና ሰብአዊ ፍጡር ላይ ወንጀል በመፈጸም ቀድሞ የኮንጎ ምክትል ፕሬዚደንት ዣን ፔሬ ቢምባ ላይ ዛሬ ብይን አስተላፏል። ዘጋቢያችን ሪቻርድ ግሪን ያጠናቀረዉን ጽዮን ግርማ ታቀርባለች።

ሦስት አባላት ያሉት የዳኞች ሸንጎ ባሳለፍው ውሳኔ እ.አ.አ ከ2002 እስከ 2003 ዓ.ም. በማዕከላዊት አፍሪካ ሪፐብሊክ ውስጥ ሚሊሺያዎቻቸው ለፈጸሙት ግድያ አስገድዶ መድፈርና ዝርፊያ ቢምባ ኃላፊ ናቸው ሲል ፈርዷል። የኮንጎ ነጻነት ንቅናቄ የተባለው የዣን ፔሬ ቢምባ ድርጅት የማዕከላዊ አፍሪካ ፐሬዚዳንት የአንጄ ፌሌክስ ተዋጊዎችን ይረዳ ነበር።

ብይኑን ያነበቡት ብራዚላዊት ዳኛ ሲልቫ ስቴነር የቢምባ ወታደሮች ሆን ብለው የማዕከላዊት አፍሪካ ዜጎችን ኢላማ በማድረግ በሴቶች ፣ሕፃናትና አረጋዊያን ጭምር ጥቃት እንዳደርሱ መረጃ አለ ብለዋል።

ዘጋቢያችን ሪቻርድ ግሪን ያጠናቀረዉን ጽዮን ግርማ ታቀርባለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምፅ ያድምጡ።

አይሲሲ በቀድሞ የኮንጎ ምክትል ፕሬዚደንት ቢምባ ላይ ብይን ሰጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:13 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG