በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታሪካዊ ቅርሶች በማውደም የተከሰሰው አህመድ አል-ማህዲ አል-ፋቂ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ቀረበ


ታሪካዊ ቅርሶች በማውደም በዐቃቤ-ህግ የተከሰሰው አህመድ አል-ፋቂ አል-ማህዲ
ታሪካዊ ቅርሶች በማውደም በዐቃቤ-ህግ የተከሰሰው አህመድ አል-ፋቂ አል-ማህዲ

ታሪካዊ ቅርሶች በማውደም በዐቃቤ-ህግ የተከሰሰው አህመድ አል-ማህዲ አል-ፋቂ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አይሲሲ (ICC)ላይ ቀረበ።

በማሊው ታሪካዊ የሃይማኖት ስፍራ ቲምቡክቱ ውስጥ ውድመት ፈጽሟል የተባለ አንድ አክራሪ የእስልምና እምነት ተከታይ ዛሬ ማክሰኞ በዓለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መቅረቡ ተነገረ።

መተኪያ የማይገኝላቸውን ታሪካዊ ቅርሶች በማውደም በዐቃቤ-ህግ የተከሰሰው አህመድ አል-ማህዲ አል-ፋቂ የተባለው ይኸው ግለሰብ፣ ዛሬ በሄግ በሚገኘው ችሎት ፊት ከመቅረቡ አስቀድሞ አጭር ቃል መናገሩም ተገልጧል።

አል-ማህዲ፣ ከአል-ቃዒዳ ጋር የሚሠራው የአንሳር ዲን Ansar Dine ነውጠኛ ቡድን አባል እንደነርም ታውቋል።

ሰሜናዊ ማሊን ይቆጣጠር የነበረው የአንሳር ዲን ነውጠኛ ቡድን፣ በፈረንሳይ ወታደራዊ ኃይሎች እአአ በ2012 መወገዱ አይዘነጋም። ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሶችን ይሁነኝ ብሎ በማውደም ወንጀል አይሲሲ(ICC) ላይ የቀረበው የመጀመርያ ተከሳሽ አል-ማህዲ መሆኑ ነው።

ታሪካዊ ቅርሶች በማውደም የተከሰሰው አህመድ አል-ማህዲ አል-ፋቂ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:47 0:00

XS
SM
MD
LG