በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳኑ ፕረዚዳንትና በአለም አቀፍ የወንጀል ችሎት መካከል የሚታየው ፍጥጫ


Sudanese President Omar AL-Bashir
Sudanese President Omar AL-Bashir

የሱዳን ፕረዚዳንት ዑመር ዐል-ባሽር በአፍሪቃ ህብረት ጉባኤ ለመገኘት የአለም አቀፍ የወንጀል ችሎት ውል ፈራሚ በሆነችው ደቡብ አፍሪቃ ገብተው ባለፈው ሰኞ በሰላም ለመመለስ የቻሉት አንድ የደቡብ አፍሪቃ ፍርድ ቤት የሱዳኑ ፕረዚዳንት ከደቡብ አፍሪቃ እንዳይወጡ ባዘዘበት ወቅት መሆኑ ይታወቃል። አቶ ነጻነት ደምሴና ዶክታር ኢስኪኤል ጋቢሳ ስለጉዳዩ ሃሳባቸውን እንዲሰጡ ጋብዘናል።

የደቡብ ሱዳን ፕረዚዳንት ዑመር ዐል-ባሽር በአፍሪቃ ህብረት ጉባኤ ለመገኘት የአለም አቀፍ የወንጀል ችሎት ውል ፈራሚ በሆነችው ደቡብ አፍሪቃ ገብተው ባለፈው ሰኞ በሰላም ለመመለስ የቻሉት አንድ የደቡብ አፍሪቃ ፍርድ ቤት የሱዳኑ ፕረዚዳንት ከደቡብ አፍሪቃ እንዳይወጡ ባዘዘበት ወቅት ነው።

ቀደም ሲልም የደቡብ አፍሪቃው ገዢ ፓርቲ የአፍሪቃ ብሄራዊ ኮንግረስ ችሎቱ በአፍሪቃውያን ላይ በጎ አመለካከት የለውም። ስለሆነም ለተመሰረተበት አላም ጠቃሚነቱ አብቅቷል የሚል መግለጫ አውጥቶ እንደነብር ተዘግቧል። ይህን መሰረት በማድረግም በጉዳዩ ላይ ሃሳባቸውን እንዲገልጹልን ሁለት ምሁራንን አነጋግረናል። አቶ ነጻነት ደምሴ በደቡብ አፍሪቃ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የሰብአዊ መብት ጉዳይ ጥናትና ምርምር ሃላፊ ናቸው። ዶክታር ኢስኪኤል ጋቢሳ ደግሞ በሚችጋን ክፍለ-ግዘት በሚገኝ ኬተሪንግ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪቃ ጉዳዮችና የኢኮኖሚ ታሪክ አስተማሪ ናቸው።

በደቡብ አፍሪቃ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የሰብአዊ መብት ጉዳይ ጥናትና ምርምር ሃላፊ አቶ ነጻነት ደምሴ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ፕረዚዳንት ዑመር ዐል-ባሽር ደቡብ አፍሪቃ እንደገቡ ከአይሮፕላን ማረፍያው ታስረው ወደ አለም አቅፍ ፍርድ ቤት መላክ ነበረባቸው የሚል አቋም እንዳለው ገልጸዋል።

ዶክተር ኢስቂኤል ጋቢሳ ደግሞ የአፍሪቃ ህብረት የአለም አቀፍ የወንጀል ችሎት ክስ በአፍሪቃ መሪዎች ላይ ያተኮረ ነው። ሌሎቹን የአለም ግዛቶች በሚገባ አይመለከትም በሚል በአፍሪቃ መሪዎች ላይ የሚቀርበውን ክስ ስራ ላይ እንደማያውል። አባል ሀገሮቹም ስራ ላይ እንዲያውሉ እንደማያስገድዳቸው መግለጹን አስረድተዋል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:18:01 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG