በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዋሺንግተንን አካባቢዋ ኢትዮጵያዊያን ለተራቡ መርጃ ድጋፍ አሰባሰቡ

በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ኢትዮጵያ ውስጥ በደረሰው ድርቅ ምክንያት ለተፈጠረው የምግብ እጥረት ድጋፍ ለመላክ የሚያስችል ገንዘብ ለማሰባሰብ ተገናኝተው ነበር።

“የዓለም እጆች ወደ ኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በተሠናዳው ስብሰባ ላይ በሙያዊ መንገድ የተካሄዱ ጥናቶች ውጤት ቀርቧል።

የተራቡ ሕፃናት፣ ነፍሰጡሮችና አጥቢ እናቶች ቁጥር ቀርቧል።

አንድ መቶ ዶላር ምን ማድረግ እንደሚችል በዝርዝር ተነግሯል።

የዋሺንግተንን አካባቢዋ ኢትዮጵያዊያን ለተራቡ መርጃ ድጋፍ አሰባሰቡ
የዋሺንግተንን አካባቢዋ ኢትዮጵያዊያን ለተራቡ መርጃ ድጋፍ አሰባሰቡ

ኢትዮጵያ ውስጥ ምላሽ በመስጠት ላይ ለተሠማሩ ድርጅቶች ኮሚቴው ደብዳቤ ልኮ መልስ ማግኘቱን ኮሚቴው አስታውቋል።

በዕለቱ በተለያዩ መንገዶች፤ ከቲኬት ሽያጭ፣ በኢንተርኔት ከተሰበሰበ፣ ከቀጥታ ልገሣ፣ ከንግድ ድርጅቶች፣ ከደብረ ገነት መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስትያንና በሥሯ ካሉ ተቋማትና ማኅበራት የተገኘው ድጋፍ በግርድፉ ከ140 ሺህ ዶላር በላይ መሆኑን የኮሚቴው የሂሣብ ሹም አቶ ሰሎሞን ከበደ ለተሰበሰው ሰው ገልፀዋል።

የዋሺንግተንን አካባቢዋ ኢትዮጵያዊያን ለተራቡ መርጃ ድጋፍ አሰባሰቡ
የዋሺንግተንን አካባቢዋ ኢትዮጵያዊያን ለተራቡ መርጃ ድጋፍ አሰባሰቡ

የኮሚቴው ዓላማ በጠቅላላው አንድ ሚሊየን ዶላር ማሰባሰብ መሆኑን የጥናትና መረጃ ቡድኑ መሪ ዶ/ር ሰሎሞን ገብሩ አስረድተዋል።

ገንዘብ የማሰባሰቡን ሥራ በአዳራሹ ውስጥ የመሩት የደብረ ገነት መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ ቀሲስ ዶ/ር ዘበነ ለማ ናቸው።

የዋሺንግተንን አካባቢዋ ኢትዮጵያዊያን ለተራቡ መርጃ ድጋፍ አሰባሰቡ
የዋሺንግተንን አካባቢዋ ኢትዮጵያዊያን ለተራቡ መርጃ ድጋፍ አሰባሰቡ

“እንዲህ ዓይነቱ እንቅስቃሴ ችግር ከሃገር እስኪጠፋ መቀጠል እንዳለብን እየተነጋገርን ነው” ብለዋል ከሃሣቡ ጠንሣሾችና ከኮሚቴው አባላት አንዱ የሆኑት አቶ ገብረየስ ቤኛ።

የዋሺንግተንን አካባቢዋ ኢትዮጵያዊያን ለተራቡ መርጃ ድጋፍ አሰባሰቡ
የዋሺንግተንን አካባቢዋ ኢትዮጵያዊያን ለተራቡ መርጃ ድጋፍ አሰባሰቡ

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የዋሺንግተንን አካባቢዋ ኢትዮጵያዊያን ለተራቡ መርጃ ድጋፍ አሰባሰቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:19 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG