አዲስ አበባ —
በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሲቲ ዞን በድርቁ ምክንያት ከወር በፊት ተከስቶ የነበረዉ አደጋ እንዳይደገም ለፌዴራል የአደጋ መካከል ዝግጁነትና የምብ ዋስትና ዘርፍ ያሳታወቁ መሆናቸዉን ከዞኑ ሕዝብ የተሰየመ ኮሚቴ አባላት እንደሆኑ የሚናገሩ ሰዎች ገለጹ።
በአካባቢዉ የሚሰጠዉ የእህል እርዳታ በቂ እንዳልሆነና ለአንዳንድ አካባቢዎች ጭራሽ እርዳታ እንዳልተሰጠ አስታዉቀዋል።
የችግሩ ዋና መንስኤም የመልካም አስተዳደር እጦት ነዉ ብለዋል የኮሚተዉ አባላት።
ዝርዝሩን መለስካቸዉ አመሃ የላከዉን ዘገባ ያቀርባል። ዝርዝሩን ከዚህ በታች ያድምጡ።