ለኤርትራ ቅርብ በሆነችው የኢትዮጵያ ድንበር ላይ በምትገኘው በሽሬ 3 የስደተኞች መጠለያ ይገኛል። ሺምበላ፣ማይ-አኒ፣አዲ-ሃሩሽ በተሰኙት በ እነዚህ የመጠለያ ቦታዎች መሰረታዊ የሆነውን የምግብ፣ የጊዜያዊ መጠለያ፣የውሃ፣ እንዲሁም የህክምና አገልግሎት ስደተኞቹ እንዲያገኙ ይደርጋል።
በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በቨርጂኒያ ነዋሪ የሆነች አንዲት ወጣት እንግዳችን ናት። ዳናይት ፀጋዬ ትባላለች። የትውልድ ሃገሯ በኤርትራ ሰናአፌ ነው። የ11 አመት ልጅ ሳለች አባቷን ፍለጋ ወደ ኢትዮጵያ ከናቷና ከታናናሽ 3 እህቶቿ ጋር በእግርና በመኪና ተጉዘው ዛላ አንበሳ ኢትዮጵያ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ለሁለት አመታት ኖረዋል።
ዳናይት በአሁኑ ሰዓት በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የኮሌጅ ተማሪ ናት ። ያለፈችበትን የህይወት ተሞክሮ ለታናናሾቿ ትምህርት ይሆን ዘንድ ትመክራለች። በቤት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በምትማርበት ኮሌጅም እንዴት ስኬትን ማምጣት እንደሚቻል ተሞክሮዋን ታካፍላለች። በተጨማሪም ልጆችን በትምህርታቸው ብልጫን እንዲያመጡ ብቻ ሳይሆን እንዴት የተማሩትን እንደሚተገብሩ ደጋግሞ መንገር ለወደፊት የህይወት ስኬታቸው አስፈላጊ ነው ትላለች። ከመስታወት አራጋው ጋር ያደረገችውን አጠር ያለ ቆይታ ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያዳምጡ።