በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የኢትዮጵያ ባህል ሊጠፋ አይገባውም!” ኢትዮ-ጀርመናዊው አሮን ጌታቸው


ፋይል ፎቶ አሮን ጌታቸው
ፋይል ፎቶ አሮን ጌታቸው

አሮን ጌታቸው ይባላል። የ17 አመት ወጣት ነው። የመድረክ ተዋናይና የቀልድ ሰው መሆን ይፈልጋል። የሚኖረው ከኢትዮጵያ ርቆ ቢሆንም ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ብቻ ደስታው የላቀ ነው።

ተወልዶ ያደገው በጀርመን ሀገር ፍራንክፈርት ሲሆን በጀርመኖችና በኢትዮጵያውያን መካከል ያለውን ልዩነት የሚያስገርመውንና የሚያስቀውን ለሌሎች ኢትዮጵያውያን በቀልድ መልክ በማቅረብ ብዙዎችን ያዝናናል፤ አድናቆትንም አትርፏል። ቁጥራቸው በርካታ ከሆኑ ጀርመናውያን ጋር ለትወና የትምህርት ዕድል ተወዳድሮ ለትምህርት ከተመረጡት አስር ወጣቶች መካከል አንዱም ሆኗል አሮን።

እንዴት ወደ ቀልድ እንደገባ ሲናገር በሚኖርበት በፍራንክፈርት ከተማ የተመለከተውን የአበሻ ባህል፣ እምነትና ልምድ በአካባቢው ለሚያገኛቸው ሀበሾች መናገር ሲጀምር ይስቁ ጀመር። “ከአበሻ ባህል የሚገርመኝ ነፋስን ወይም ብርድን ለምን አንደሚፈሩትና ስለብርድ ያላቸው አመለካከት ነው… በጣም ነው የሚያስቀኝ። ከጀርመኖቹ ደግሞ ለሰው የሚሰጡት አክብሮት በፍፁም ከኢትዮጵያ ባህል የራቀ መሆኑ ያስገርመኛል።” ይላል አሮን።

ከመስታወት አራጋው ጋር አጠር ያለ ቆይታን አድርገዋል።ሙሉ ጨዋታውን ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያዳምጡ።

“የኢትዮጵያ ባህል ሊጠፋ አይገባውም!” ኢትዮ-ጀርመናዊው አሮን ጌታቸው።
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:17 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አሮን ጌታቸው በመድረክ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:47 0:00

XS
SM
MD
LG