እ.አ.አ 2012 የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ቆጠራ እንደሚያመለክተው ወደ 251 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካን ሃገር ይኖራሉ። ይህም በነዋሪው ቁጥር ብዛት የተነሳ ከናጄሪያ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ እንዲቀመጥ አድርጎታል።
በካሊፎርኒያ፣ ሚኒሶታና ቴክሳስ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ፤ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ (ሜሪላንድ አና ቨርጅንያ) ካለው 35ሺህ ነዋሪ ጋር ግን ሊወዳደር አይችልም። ከዚህ ቁጥር ውስጥ 87% የሚሆነው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከ18 አመት እድሜ በታች ሲሆን 18 ፐርሰንቱ ደግሞ 18-64 የእድሜ ክልል ውስጥ ይገኛል። ከጠቅላላው የዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪ ህዝብ ውስጥ 0.5% የሚሆነው ደግሞ ወጣት ትውልደ ኢትዮጵያዊ ነው።
ሐምራዊት ተስፋ በአሜሪካ መኖር የጀመረችው የ15 አመት ሳለች ጀምሮ ነው። በልጆችና በቤተሰብ ግንኙነት ላይ በመስራት ላይ ትገኛለች። የከፍተኛ ትምህርቷንም ያጠናቀቀችው በማህበራዊ ጉዳይ ሰራተኝነት ላይ ነው። “ልጅን ማሳደግ በምዕራብ ሃገሮች” የተሰኘ ኢትዮጵያዊነቱን ሳይለቅ ከአሜሪካ ባህል ጋር አጣጥሞ ልጅን እንዴት ማሳደግ እንደሚቻል መፅሃፍ በማሳተም በአሜሪካን ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወላጆች አቅርባለች።
በአሜሪካን ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚታየውን የባህል ግጭት እንዲህ ትገልፀዋለች። ከመስታወት አራጋው ጋር ያደረገችውን ቆይታ የተያያዘው ድምፅን በመጫን ያድምጡ።