አዲስ አበባ —
በኢትዮጵያ 27ኛዉ የድል የአልማዝ ኢዮበልዩ ተከብሮ ዋለ
አርበኞች
ሚያዝያ 27 ቀን የጠላት ባንዲራ ተወግዶ ያገራችን ሰንደቅ አላማ የተውለበለበበት ዕለት በመሆኑ በታላቅ ኩራት የምናከብረው ብሄራዊ በአላችን ነው ሲሉ የኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ተናገሩ።
መልካም አርያነቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ መተላለፍ እንዳለበትም አስገነዘቡ። ለሃገር ሉአላዊነትና ነፃነት በተደጋጋሚ ቃል የሚገባበት ልዩ የታሪክ ቀን ነው ሲሉም አሳስበዋል።
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት በበኩላቸው የአንድ አባት አርበኛ መታሰቢያ ሃውልት በቅርቡ እንደሚመረቅ አበሰሩ።
የእለቱ ታሪካዊነት በወጣቱ ትውልድ ዘንድ እንደማይታወቅም አስተያየቶች አሉ።
የድምጽ ፋይሉን በመጫን የመለስካቸው አመሃን ዘገባ ያድምጡ።
ለመሆኑ እንደዚህ አይነት ታሪካዊ ድሎች በአሁኑ ትውልድ ህይወት ውስጥ ምን ቦታ አላቸው? ሔኖክ ሰማእግዜር አንዳንድ ወጣቶችን አነጋግሯል።
-
ሔኖክ ሰማእግዜር