በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአድዋ ድል ለጥቁር ህዝቦች ያበረከተው አስተዋጽዖ


የዛሬ 115 ዓመት በቅኝ ገዥ የአውሮፓ ወታደሮች ላይ አፍሪካዊያን ከፍተኛ ድል ተቀዳጁ።

በወራሪው የጣሊያን ጦር ላይ የኢትዮጵያው ንጉስ ሚኒሊክ ድል አድራጊ ክንዳቸውን ሲያሳርፉ፤ በመላው አለም ጥቁር ህዝቦች በባርነትና በቅኝ ግዛትላይ ነበሩ።

የአድዋ ድል ለኢትዮጵያ ነጻነትና ኩራትን፤ በአለም ዙሪያ በተለይ በአሜሪካዎቹ ሰፋፊ እርሻዎች ለ500 አመታት በባርነት የተጋዙ ጥቁር ህዝቦች ዘንድ ደግሞ፤ የማንነት ማረጋገጫ፣ የዘመናት ጭቆናና የስነ-ልቦና ቁስልን አውልቆ የመጣያ የተስፋ ትንሳኤ ነበር።

የካቲት 23 1888ዓም በዘመኑ ሃያላን ከነበሩ የአውሮፓ ሃያላን አንደኛው የሆነው የጣሊያን ጦር በአድዋ ድል ተመትቷል።

በዚያን ዘመን አውሮፓዊያን በበርሊን አፍሪካን ለመቀራመት በበሊን ጀርመን በተፈራረሙት ስምምነት ማግስት፤ አፍሪካዊያን ከውጭ ወራሪዎችና እርስ-በርሳቸው መፋጀት የጀመሩበት ጊዜ እንደሆን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።

በዚያ ጊዜ በተናጠል በንጉሶችና በጭፍራ አለቆች ለየብቻ ከአውሮፓዊያኑ ጋር የተደረጉ ውጊያዎች በሰሜን፣ በደቡብ በምስራቅና በምእራብ አፍሪካ ትርጉም ያለው ስኬት ሳይኖራቸው፤ አፍሪካዊያን በቅኝ ግዛት መውደቅ የጀመሩበት ጊዜ ነበር።

ዘመናዊ መሳሪያ የጣጠቀው የጣሊያን ጦር ወደ ኢትዮጵያ የቅኝ ግዛት ተልእኮውን ይዞ የመጣው በአስር ሽዎች የተቆጠሩ በአግባቡ የሰለጠኑ ወታደሮችን ይዞ ነው። ነገሩ እንደታቀደው ሳይሆን ቀርቶ የጣሊያን ጦር በአድዋ ተሸነፈ።

አውዋ ኢትዮጵያዊያን ለሚቀጥሉት ዘመናት ነጻ ሀገርና ጠንካራ መንፈስ ያላቸው አፍሪካዊያን የሚኖሩባት ግዛት ተደርጋ እንድትታይ ረድቷል። ከኢትዮጵያ አልፎ፤ የአድዋ ዜናና በተከታይነት አገሪቱ የንጉሳዊ ስርዓቷን ጠብቃ በመኖሯ፤ የጥቁር ህዝቦች ኩራት ሆኗል ይላል የታሪክ ተማሪ የሆነው ክንዴነህ እንደግ።

በሴይንት ቶማስ ዩ.ሴስ. ቨርጂን አይላንድስ የሚገኝ የራስ ተፈሪያን ቤት
በሴይንት ቶማስ ዩ.ሴስ. ቨርጂን አይላንድስ የሚገኝ የራስ ተፈሪያን ቤት

በዚያን ጊዜ በዘር መገለል ይደርስባቸው የነበሩ ጥቁር ህዝቦችና በቅኝ ግዛት የነበሩን ጨምሮ፤ ከሀይማኖት መጻህፍትም ሳይቀር እየተጠቀሰ፤ ባርነት ከዱሮች የነበረ እንጂ አሁን ያለው የቅኝ ገዥ ሃይላ የፈጠረው ስርዓት እንዳልሆነ ይነገር ነበር።

በዚህና ለ500 ዓመታት በደረሰባቸው ጥቃት ማንነታቸውን ይጠራጠሩ፤ የሰውነት ደረጃቸውን ዝቅ አድርገው ይመለከቱ የነበሩ ህዝቦችን ከዚህ አመለካከት እንዲላቀቁ ማድረግ ከባድ ነበር።

ባርነት በአዋጅ እንዲቀር ከተደረገም በኋላ፤ ጥቁሮች እስከ ዛሬ ድረስ የእኩልነት መብቶቻቸው እንዲከበሩ ይታገላሉ።

ዛሬ ዛሬ ብዙ ተስፋዎች አሉ፤ አሜሪካ ጥቁር ፕሬዝደንት መርጣለች፤ አፍሪካዊያንም እራሳቸውን ያስተዳድራሉ። ያኔ የተስፋ ጭላንጭል በሌለበት ዘመን ኢትዮጵያና የአድዋ ድል ፍሬ ለጥቁር ህዝቦች መጽናናት ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የስነ-ልቦና በመረታታ ሆኗቸዋል።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG