ዋሽንግተን ዲሲ —
ነገ ፻፳ኛው(120ኛው) የዓድዋ ድል በዓል ይከበራል፡፡ በሰሜን አሜሪካ በሜሪላንድ ክፍለ ግዛት በርካታ ኢትዮጵያዊያን የሚኖሩበት ሞንትጎመሪ አውራጃ (Montgomery county) መጋቢት ወር የዓድዋ ድል በዓል ኾኖ እንዲታሰብ ወስኗል። ይህን ወሳኔ እንዲሰጥ ያስቻለውም የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማኅበረሰብ(Ethiopian Heritage Society in North America (EHSNA) ድርጅት ነው።
የኢትዮጵያዊነት ውርስና ቅርስ ማኅበረሰብ(Ethiopian Heritage Society in North America (EHSNA) ድርጅት ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ካሌብ አማረና በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ብሥነ ጥበባት ኮሌጅ በአለ ሥነጥበባት ትምሕርት ክፍል የኢትዮጵያ ታሪክና ሥን ጥበብ መምሕር የኾኑት አቶ አበባው አያሌው ስለ ዓድዋ ድል ጥቂት ብለዋል፡፡
ይህንኑ በተመለከተ ጽዮን ግርማ ተከታዮን ዘገባ ታቀርባለች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ
በኢትዮጵያስ?
የዓድዋ በዓል በኢትዮጵያ ተገቢውን ክብር አግኝቶ እየተከበረ ነው?
ጽዮን ግርማ ባለሞያዎችን አነጋግራ በነገው ዕለት ዝግጅት ይዛ ትቀርባለች፡፡