ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
የወባ ወረርሽኝ በዓለም ዙሪያ በእጅጉ ቢቀንስም አሁንም ቢሆን በየዓመቱ ሁለት መቶ ሚሊየን ሰው እንደሚያዝ የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡
ዛሬም ቢሆን በዓመት ከስድስት መቶ ሺህ በላይ ሰው እንደሚሞትም ድርጅቱ የዘንድሮን የወባ ቀን አስታክኮ ባወጣው ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
በሌላ በኩል ግን ኢትዮጵያ ላለፉት አምስትና ስድስት ተከታታይ ዓመታት የወባ ወረርሽን ተከስቶባት እንደማያውቅ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሃገርአቀፍ የወባ መከላከያ መርኃግብር አስተባባሪ ወ/ት ሕይወት ሰሎሞን ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ በወባ የመያዝ አጋጣሚ በ67 ከመቶ መቀነሱን፣ የሞት መጠኑ በ48 ከመቶ መውረዱንና ዕድሜአቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት የወጣ ሞት መጠን በ81 ከመቶ ማሽቆልቆሉን አስረድተዋል፡፡
ከኢትዮጵያ አጠቃላይ ስፋት 75 ከመቶ የሚሆነው ለወባ ተጋላጭ መሆኑንና ከሕዝቧም 60 ከመቶው የሚኖረው በወባማ አካባቢዎች እንደሆነ ወ/ት ሕይወት ሰሎሞን ገልፀዋል፡፡
ለተጨማሪ ዝርዝር የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡