በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የወባና የትራኮማ ቀን በአማራ


በአማራ ክልል ሰባተኛው ዙር የወባና የትራኮማ ዕለት ተከብሯል፡፡ በሚሊዮኖች ለሚቆጠር ሰው የወባና የትራኮማ መድኃኒቶች ለሰባት ቀናት ይታደላሉ፡፡

በደቡብ ወሎና በደቡብ ጎንደር አንዳንድ ወረዳዎችም በተገኘው መልካም ውጤት ምክንያት ከዚህ ዘመቻ ውጭ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ከጎንደር ከተማ 42 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘት በማክሰኚት ከተማ በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የካርተር ማዕከል የኢትዮጵያ ቢሮ ተጠሪ ዶ/ር ዘርይሁን ታደሰ በአማራ ክልል የነበረውን የትራኮማ ችግር በአምስት ዓመታት ውስጥ በሃያ አምስት ከመቶ መቀነስ መቻላቸውን አመልክተዋል፡፡

ከሁለት ወራት ጀምሮ ሕዝቡ ሕክምና እንዲያገኝ በማክሰኚት ቅስቀሣ ሲያደርጉ ከነበሩ የበጎ ፍቃድ ተሣታፊዎች አንዱ የሆኑት አቶ ዓለም ሃሰን ሲናገሩ በቅስቀሣቸው ምክንያት ሕዝቡ ወደማዕከሉ እየቀረበ ክትባት እየወሰደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዘመቻውን በመተባበር እያካሄዱ ያሉት ዓለምአቀፉ የትራኮማ ኢኒሺየቲቭ፣ ካርተር ማዕከልና የአማራ ጤና ቢሮ እንደሚሉት ካለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 25 ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት ቀናት ከአሥር ሚሊየን በላይ ሕዝብ በወባና በትራኮማ ላይ ያተኮረ ሕክምናና አገልግሎት ያገኛል፡፡

መለስካቸው አምሃ ከባህርዳር ያጠናቀረውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG