በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሃያ ሁለቱ ፓርቲዎች ክርክርና ድርድርን በማስመልከት ከዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር የተደረገ ቆይታ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

በገዥው ፓርቲና በሀገር አቀፍ ፓርቲዎች መካከል ሊካሄድ የታቀደው ድርድር በበርካታ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ተስፋቸውን ገልፀዋል፡፡

በገዥው ፓርቲና በሀገር አቀፍ ፓርቲዎች መካከል ሊካሄድ የታቀደው ድርድር በበርካታ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ተስፋቸውን ገልፀዋል፡፡

በተደራዳሪዎች ፓርቲዎች ብቻ ሊወሰኑ የማይገባቸው እና የሕዝቡን ይሁንታ ጭምር የሚጠይቁ ጉዳዮች ሊኖሩም እንደሚችሉም ጠቁመዋል፡፡

ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ እና ሃያ አንድ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎች ለድርድር የሚያደርጉትን ዝግጅት ቀጥለዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች የክርክርና የድርድር የአሠራር ረቂቅ ደንብ በሚባለው ሰነድ ላይ የሚያደርጉት ውይይትም አልተቋጨም፡፡ እናም ተደራዳሪዎቹ በየትኞቹ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩሩ ገና አልተወሰነም፡፡ የአብላጫ ድምፅ ሥርዓት የሚባለውን የምርጫ ሥርዓት ማሻሻል አንዱ ነጥብ ሊሆን እንደሚችል የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት እና የግል የፓርላማ አባል ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይገምታሉ፡፡

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ያነጋገራቸው እስክንድር ፍሬው ተከታዩን ልኳል፡፡

የሃያ ሁለቱ ፓርቲዎች ክርክርና ድርድርን በማስመልከት ከዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ጋር የተደረገ ቆይታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:48 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG