በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ድምጼን በመስጠት ብሄራዊ ግዴታዬን ተወጥቻለሁ" - የጂቡቲ ፕሬዘደንት


ፋይል ፎቶ - የጂቡቲ ፕሬዘደንት ኢስማኢል ኦማር ጉሌህ
ፋይል ፎቶ - የጂቡቲ ፕሬዘደንት ኢስማኢል ኦማር ጉሌህ

በድምጽ መስጫ ጣቢያዎች አካባቢ የነበረው ድባብ ሰላማዊ እንደነበር አንዳንዶቹ ድምጽ ሰጪዎች ሲናገሩ ብዛት ያለው ወታደር አይተናል ያሉም አሉ።

ዛሬ ዓርብ ጅቡቲ ውስጥ ፕሬዚደንታዊ ምርጭ እየተካሄደ ነው። ቁጥራቸው ወደ 190,000 የሚጠጋ ድምጽ ሰጪዎች ከቀረቡት ስድስት ተፎካካሪዎች መሃል ይመርጣሉ።

የሃገሪቱ ፕሬዝደንት ጌሌ ዛሬ ጠዋት ጅቡቲ ከተማ ድምጽ የሰጡ ሲሆን “ድምጼን በመስጠት ብሄራዊ ግዴታዬን ተወጥቻለሁ። ድምጼን የሰጠሁት ለራሴ ነው። አብዛኛው ህዝብም ይህንኑ እንደሚያደርግ ተስፋ አለኝ“ ብለዋል።

በድምጽ መስጫ ጣቢያዎች አካባቢ የነበረው ድባብ ሰላማዊ እንደነበር አንዳንዶቹ ድምጽ ሰጪዎች ሲናገሩ ብዛት ያለው ወታደር አይተናል ያሉም አሉ።

ፋይል ፎቶ - የጂቡቲ ፕሬዘደንት ኢስማኢል ኦማር ጉሌህ
ፋይል ፎቶ - የጂቡቲ ፕሬዘደንት ኢስማኢል ኦማር ጉሌህ

ተቃዋሚ መሪዎች ሂደቱ ተዛብቷል ሲሉ ከወዲሁ ሲያማርሩ ቆይተዋል። መንግስቱ ሁለት ተወካዮቻችንን ከድምጽ መስጫ ጣቢያ አስወጥቶብናል ሲሉ ሁለት ተቃዋሚ መሪዎች ከሰዋል።

እ.አ.አ. ከ1999 ጀምረው ስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚደንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ እንደሚያሸንፉ በብዙዎች የሚጠበቅ ሲሆን የምርጫው ውጤት ነገ ቅዳሜ ጡዋት ይፋ እንደሚሆን ተገልጿል።

VOA60 Africa - Djibouti: Voting in the presidential election is underway
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:59 0:00

XS
SM
MD
LG