በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና በጅቡቲ አንድ የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር እየገነባች ነው


ፋይል ፎቶ - የቻና መርከብ እአአ 2014 ሮይተር
ፋይል ፎቶ - የቻና መርከብ እአአ 2014 ሮይተር

ይህ በጅቡቲ እየተገነባ ያለ የጦር ሰፈር፣ ቻይና በወታደራዊ መዋቅሯ ላይ ለውጥ ማድረጓን ብቻ ሳይሆን አፍሪቃ ላይ ያላትን ትኩረትም የሚያሳይ ነው።

ቻይና፣ በምሥራቃዊቷ አፍሪቃዊት አገር ጅቡቲ አንድ የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር እየገነባች መሆኗ ተነገረ።

ቻይና በወታደራዊ መዋቅሯ ላይ ለውጥ ማድረጓን ብቻ ሳይሆን አፍሪቃ ላይ ያላትን ትኩረትም የሚያሳየው ይህ ጦር ሰፈር፣ ለቻይና የመጀሪያው የውጪ አገር ወታደራዊ ሰፈር መሆኑ ነው።

ቻይና ለአፍሪቃ ተጨማሪ የ$60 ቢልዮን (Billion) ርዳታ ለመስጠት ቃል መግባቷም ታውቋል። ጂቡቲ ከመካከለኛው ምሥራቅ የሚነሱ የንግድ ዝውውሮችን ለመቃኘት ስትራተጃክ ስፍራ ሆና ተገኝታለች።

ቻይና፣ ቀደም ሲል ጅቡቲ ውስጥ ጦር ሰፈር ካላቸው ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ከፈረንሳይና ከጃፓን አንዷ መሆንዋ ነው እንግዲህ።

XS
SM
MD
LG