በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ፣ጅቡቲና ቻይና በጋራ የነዳጅ ፍለጋ ግንባታ ስራ ላይ ተስማሙ


የጅቡቲ ካርታ
የጅቡቲ ካርታ

ጅቡቲ ስፋቷ አነስተኛ ቢሆንም ለቀይ ባህር ባላት የወደብ ቅርበት በብዙዎች የውጭ ባለሃብቶች ንግድ እንቅስቃሴ ተፈላጊ ያደርጋታል።

ባለፈው ሳምንት የጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር፤ በኦጋዴን ለታቀደው የነዳጅ ማውጣት ስራ መጀመር የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። ይህ ግንባታ ጋዝን ወደ ፈሳሽነት የሚቀይር ፋብሪካን የሚጨምር ነው።የግንባታው ስፍራም ከጅቡቲ 16 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ነው።

ከኢትዮጵያ እስከ ጅቡቲ ወደብ ወደ 800 ኪሎሜትር የሚጠጋው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ መዘርጋትም በስምምነቱ ተካቷል።

የዚህ ግንባታ ስራ ወደ 4 ቢልየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚፈጅ የጅቡቲው የተፈጥሮ ሃይል ሚኒስትር አቶ አሊ ያኮብ ማህሙድ ገልፀዋል።

Poly-GCL የተባለው ስምምነቱን የፈረመው የቻይና ድርጅት ለግንባታው የሚያስፈልገውን ወጪ እንደሚሸፍንና ነዳጁ ወደ ቻይና እንደሚላክ አስታውቋል።

ይህ የነዳጅ ፍለጋ ስራ፤ ጅቡቲ ከአንድ የቻይና የግል ድርጅት ጋር ያደረገችው ስምምነት ነው። በእቅዱ መሰረት ከተከናወነ እ.አ.አ 2018 የግንባታው ስራ ተጠናቆ ነዳጅ የማውጣት ስራው ይጀመራል። የጅቡቲው የተፈጥሮ ሃይል ሚኒስትር ይህ ለሃገሪቱ የመጀመሪያው ከፍተኛውና የግል ፕሮጀክት እንደሆነ ተናግረዋል።

በሌላ ወገን የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር በመባል የሚታወቀው ONLF አማፂ ቡድን ግንኙነት ሃላፊ አብድራህማን ማሃዲ የተደረገው ስምምነት ተቀባይነት የለውም ብለዋል። እሳቸው እንደሚሉት ስምምነቱ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑትን የደቡብ ኦጋዴን ጎሳዎችን አላካተተም። ስለዚህ መቀጠል የለበትም ብለዋል።

ከኢትዮጵያ መንግስት እስከአሁን ምንም አይነት መግለጫም ሆነ አስተያየት ስለስምምነቱ አልተሰጠም። የቪኦኤው ሃሩፍ ማሩፍ የዘገበውን መስታወት አራጋው ታቀርበዋለች። ለማዳመጥ ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት ይጫኑ።

ኢትዮጵያ፣ጅቡቲና ቻይና በጋራ የነዳጅ ስራ ግንባታ ላይ ተስማሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:04 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG