በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኤርትራን ከሰሱ


ኢስማኤል ኦማር ጌሌ - የጅቡቲ ፐሬዚዳንት
ኢስማኤል ኦማር ጌሌ - የጅቡቲ ፐሬዚዳንት

የጅቡቲ ፐሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ኤርትራን ባልተገባ ባሕርይና በነገረኛነት ከስሰዋል፡፡

የኤርትራና የጅቡቲ ካርታ
የኤርትራና የጅቡቲ ካርታ

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የጅቡቲ ፐሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ኤርትራን ባልተገባ ባሕርይና በነገረኛነት ከስሰዋል፡፡

ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ ባደረጉት ንግግር ፕሬዚዳንቱ ይህንን ክሣቸውን ያሰሙት ፕሬዚዳንት ጌሌ “ኤርትራ ለአካባቢውና በአጠቃላይም ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ አደጋ ነች” ብለዋል፡፡

በአውሮፓ አቆጣጠር ከ2008 ዓ.ም አንስቶ የኤርትራ ወታደሮች የሰሜናዊ ግዛቶቻቸውን አንዳንድ አካባቢዎች ያለአግባብ ከተቆጣጠሩ በኋላ በዚህም ዓመት ውጥረትና ውዝግቡ መቀጠሉን የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ተናግረዋል፡፡

የመንግሥታቸው ባለሥልጣናትና እራሳቸውም በተደጋጌሚ ጉዳዩን ለማስረዳት ወደ ኒው ዮርክ መመላለሳቸውን አመልክተዋል፡፡

ሃገራቸው በሰላም፣ በሽምግልናና በድርድር እንደምታምን የተናገሩት ፕሬዚዳንት ጌሌ “የተክለ ግዛታችን የማይደፈር መሆን ግን ለድርድር የሚቀርብ አይደለም” ብለዋል፡፡

የኤርትራ መንግሥት ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ “የአካባቢው ብቸኛና ዋነኛ ያለመረጋጋት ምክንያት የኤርትራን ሉዓላዊ ግዛቶች በኃይል ይዛ ያለችው ኢትዮጵያ ናት” ብሏል፡፡

ከጅቡቲ ጋር የገቡበት የድንበር ውዝግብ ጉዳይ በጋራ ለተስማሙባቸው ሦስተኛ ወገን አካላት የቀረበ መሆኑን የኤርትራ መንግሥት ባለፈው የካቲት መጀመሪያ አውጥቶት በነበረ መግለጫ ተናግሮ የነበረ ሲሆን ንግግሩ በጥሩ ሁኔታ ተይዞ እያለ ብስለት የሌለውና በጎ መንፈስ የራቀው የጅቡቲ አቋም ለማስረዳት አስቸጋሪ ነው ብሏል፡፡

ለተጨማሪ ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ ያደረጉትን ንግግር ለመስማት ከዚህ ሥር ያለውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ፡፡

http://webtv.un.org/watch/djibouti-general-debate-70th-session/4521625112001

XS
SM
MD
LG