በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ህብረት በቡሩንዲ የሰላም ድርድር የማይካፈሉ ቡድኖች ላይ ማዕቀብ እጥላለሁ ብሏል


ፋይል ፎቶ የአፍሪቃ ሕብረት ሊቀመንበር ዶ/ር ንኮሳንዛ ድላሚኒ ዙማ [አሶሹአትድ ፕረስ/AP]
ፋይል ፎቶ የአፍሪቃ ሕብረት ሊቀመንበር ዶ/ር ንኮሳንዛ ድላሚኒ ዙማ [አሶሹአትድ ፕረስ/AP]

በሚቀጥለው ወር በሚከፈተው የቡሩንዲ የሰላም ድርድር ሳይካፈሉ በሚቀሩ የሀገሪቱ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ቡድኖች ላይ ማዕቀብ እጥላለሁ ሲል የአፍሪካ ህብረት ኣስጠነቀቀ።

በሚቀጥለው ወር በሚከፈተው የቡሩንዲ የሰላም ድርድር ሳይካፈሉ በሚቀሩ የሀገሪቱ ተቀናቃኝ የፖሌቲካ ቡድኖች ላይ ማዕቀብ እጥላለሁ ሲል የአፍሪካ ህብረት አስጠነቀቀ። ህበረቱ ሁሉም ውገኖች ልዩነቶቻቸው እንዲፈቱና ሁከቱ እንዳይባባስ እንዲከላከሉ ለማነጋገር ጥረት ይዟዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶ/ር ንኮሳንዛ ድላሚኒ ዙማ ጥቃት በሚፈጽሙ ታጣቂ ቡድኖችም ይሁን ከድርድሩ ሸምጋዮች ጋር ለመነጋገር አሻፈረን በማለት በቡሩንዲያውያን መካከል ንግግር እንዳይደረግ በሚያደናቅፍ ማናቸውም ወገን ላይ ማዕቀብ ሊጣል ይችላል ብለዋል።

የመንግስቱና የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ተወካዮች እአአ ጥር ስድስት ቀን ታንዜኒያ ኣሩሻ ላይ ተገናኝተው ሀገሪቱን ካለፈው ሚያዝያ ጀምሮ እያመሳት ያለው የፖሌቲካ ሁከት እንዳይባባስ ለመከላከል መንገድ እንዲፈልጉ ታቅዱዋል።

ይሁን እንጂ ሰኞ ዕለት ዩጋንዳ ውስጥ የተገናኙት ሁለቱ ወገኖች ልዩነቶቻቸውን እንዴት እንደሚፈቱ ኣልተስማሙም። በዚያም ላይ የሃገሪቱ መንግሥት የኣፍሪካ ህበረት ሲቪሎችን ለመጠበቅ ኣምስት ሺህ ሰላም ኣስከባሪ ሰራዊት ለማዝመት ያለውን ዕቅድ ኣልተቀበለውም።

ዛሬ የቡሩንዲ ፕሬዚደንት ፒየር ኢንኩሩዚዛ በሰጡት መግለጫ ሰላም ኣስከባሪዎቹ ካለኛ ፈቃድ ከመጡ ኣገራችን ላይ ጥቃት እንደተሰነዘረ ቆጥረን ባግባቡ ምላሽ እንሰጣለን ሲሉ ኣስጠንቅቀዋል። ሰኞ እለትም ምክትል ፕሬዚደንታዊ ቃል ኣቀባዩ ዛን ክሎድ ካርሬረዋ ሰላማ ኣስከባሪ ከመጣ እንደወራሪ ሃይል ይቆጠራል ማለታቸው ይታወሳል።

የኣፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ኤራስቱስ ሙዌንቻ ቡሩንዲ ለታቀደው የሰላም ኣስከባሪ ተልእኮ ይፋ ምላሽ ባትሰጥ ህብረት በዝምታ ሊጠብቅ ኣይችልም ፡ ህብረቱም ሆነ ኣለም ኣቀፉ ማህበረሰብ ሁኔታዎች ቢያቆለቁሉ በቸልታ ሊመለከቱ ኣይችሉም ብለዋል።

ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች የተያያዘውን ይደምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የአፍሪካ ህብረት በቡሩንዲ የሰላም ድርድር የማይካፈሉ ቡድኖች ላይ ማዕቀብ እጥላለሁ ብሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:29 0:00

XS
SM
MD
LG