በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አትሌት ኩለኒ ገልቻ በወንድ ጓደኛዋ ተወግታ ተገደለች


ሴት አትሌቶች ራሳቸውን ከእንዲህ ያለ አደጋ ለመጠበቅ የሕይወት ክህሎት ሥልጠና እንደሚያስፈልጋቸው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ የጥናት ባለሞያ አቶ ስለሺ ብስራት ተናግረዋል።

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብ ውስጥ በመካከለኛ ርቀት 800 ሜትር ተወዳዳሪ የነበረችውና በብሔራዊ ቡድን ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት ተመራጭ በመሆን የምትታወቀው የ19 አመትዋ አትሌት ኩለኒ ገልቻ ከወንድ ጓደኛዋ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በአትሌት ጓደኛዋ እጅ ህይወቷ በስለት ማለፉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ስፖርት ክለብን በምንጭነት ጠቅሶ ለአሜሪካ ድምጽ ገለፀ።

የአትሌት ኩለኒ ገልቻ ገዳይ እንደሆን የተጠረጠርው ጓደኛዋ እራሱ እጁን ለፖሊስ በመስጠቱ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እንደተጀመረ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ የጥናት ባለሞያ አቶ ስለሺ ብስራት ገልጸዋል።

አትሌቷ ለወደፊቱ በጣም ተስፋ ያላት አትሌት እንደነበረች ወጤቷ ይናገር ነበር ብለዋል። ፌደሬሽኑ በአትሌት ኩለኒ ሞት እና የአሟሟት ሁኔታ በጣም ማዘኑን አቶ ስለሺ ጠቁምው ሴት አትሌቶችን ከእንዲህ አይነት አደጋ ለመታደግ የተለየ ሥልጠና እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የአትሌት ኩለኒ ገልቻ አስከሬን በምኒሊክ ሆስፒታል ምርመራ ሲደረግለት ቆይቶ ግንቦት 5 ቀን 2008 ዓ. ም. ላይ በትውልድ አካባቢዋ ኦሮሚያ ክልል አምቦ ከተማ የቀብር ስነስርአቷ መፈጸሙ ታውቋል።

ጽዮን ግርማ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ የጥናት ባለሞያ አቶ ስለሺ ብስራትን ስለዚሁ አነጋግራ አጠር ያለ ዘገባ አሰናድታለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

አትሌት ኩለኒ ገልቻ በወንድ ጓደኛዋ ተወግታ ተገደለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:53 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG