በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ህብረት በረሃማነትን ለመዋጋት በታለመ ዕቅድ ዙሪያ የሚመክር ዓለም አቀፍ ጉባዔ በሴኔጋል በማካሄድ ላይ ነው


ጎስ ቤይዳ ተብሎ የሚጠራ በምስራቅ ቻድ በሚገኝ በርሃ ወንዝ ሰንጥቆ ያልፋል /በ2008 ዓ.ም የተነሳ ፎቶ/
ጎስ ቤይዳ ተብሎ የሚጠራ በምስራቅ ቻድ በሚገኝ በርሃ ወንዝ ሰንጥቆ ያልፋል /በ2008 ዓ.ም የተነሳ ፎቶ/

የአፍሪካ ህብረት (Great Green Wall)በግርድፉም “ታላቁ አረንጓዴ ግድግዳ” በመባል በሚታወቀውና በረሃማነትን ለመዋጋት በታለመው ዕቅድ ዙሪያ የሚመክር ዓለም አቀፍ ጉባዔ በያዝነው ሳምንት የመጀመሪያ ጉባኤውን በሴኔጋል በማካሄድ ላይ ነው። እንደ ባለ ሞያዎች አስተያየት፥ ዕቅዱ ድህነትን ለመቅረፍና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዓይነተኛ መንገድ ተደርጎ ተወስዷል።

ባለፈው ታሕሳስ ወር ፓሪስ ላይ በተካሄደው በዓየር ንብረት ለውጥ ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ጉባዔ የተሳተፉ የዓለም መሪዎች የአፍሪቃን መልክዓ ምድርና የዓየር ጠባይ ከውድመት ለማዳን በታለመ ውጥን በመጪው አምስት ዓመታት ውስጥ ለጥቅም የሚውል የ4 ቢልዮን ዶላር እርዳታ ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

ያም እርዳታ፥ በእንግሊዝኛ መጠሪያው(Great Green Wall) በግርድፉም “ታላቁ አረንጓዴ ግድግዳ” የሚል ሥያሜ ለተሰጠውና በሰሃራ እና በሰሃል የበረሃማነትን መስፋፋት ለመከላከል ከሰሃራ ደቡባዊ ጫፍ አንስቶ በአሕጉሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የደን አጥር ለማጠር የታለመውን ውጥን ማገዝ ይጨምራል።

የአፍሪካ ህብረት አርማ
የአፍሪካ ህብረት አርማ

ከሰሃራ ደቡብና ሰሜን ከሚገኙ ሃያ አገሮች የተውጣጡ፤ የመስኩ አዋቂዎችና የአነስተኛ የአካባቢ ተቋማት አባላት ያሉባቸው ልዑካን በዕቅዱ ዙሪያ ለመምከር በሴኔጋሏ ዋና ከተማ ተሰብስበዋል።

በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የባህር ዳር
በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የባህር ዳር

የሴኔጋሉ የከባቢ ሁኔታዎችና የዓየር ጠባይ ጉዳዮች ሚንስትር አብዱላየ ባቢ ባልዴ በጉባዔው መክፈቻ ባሰሙት ንግግራቸው ከዕቅዱ ጀርባ ስላለው ሃሳብ አስረድተዋል።

“'ታላቁ አረንጓዴ ግድግዳ'የደን አጥር ከማጠርም በላይ ነው፤” ይላሉ የሴኔጋሉ ሚንስትር። “የተሻለ የመሬት አጠቃቀም ብልሃትን በማስተዋወቅ የሳሃራ-ሳህል ዞን’ን ጠቀሜታ ከፍ ማድረግ ጭምር ነው።” ብለዋል።

እቅዱ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበው እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2005 ዓ.ም ሲሆን፤ በጊዜው የቀድሞው የሴኔጋል ፕሬዝዳንት አብላዪ ዋዴ የተለየ ትኩረት ሰጥተው አስተዋውቀውታል። ዓላማውም የሰሃራ በረሃ ወደ ደቡብ የሚያደርገውን መስፋፋት ለመከላከል ከሴኔጋል እስከ ጅቡቲ የሚዘረጋውን በብዙ ሺህ ኪሎ ሜትሮች የሚለካ ምድር በደንና አረንጓዴ ተክል ለመሸፈን የተያዘ እቅድ ነው።

የበረሃማነት መስፋፋትና የለም መሬት መሸርሸር በአካባቢው የደቀኑትን የምግብ እጥረትና የጸረ-ሽብር ቡድኖች መጠናከር ለመቋቋምና ብሎም የደህንነት ዋስትናን ለማረጋገጥ ጭምር ነው።

እንደ ባለ ሞያዎቹም ተጨማሪ አስተያየት፤ ጉባዔው:- ለፕሮዤው የተሰጠውን ልዩ ትኩረትና የፖለቲካ ፍቃደኝነት የሚያሳይ ነው።

አልፋ ጃሎ ከዳካር ለአሜሪካ ድምጽ ያጠናቀረውን የዚህን ዘገባ ዝርዝር አሉላ ከበደ ይዞ ቀርቧል።

የአፍሪካ ህብረት በረሃማነትን ለመዋጋት በታለመ ዕቅድ ዙሪያ የሚመክር ዓለም አቀፍ ጉባዔ በሴኔጋል በማካሄድ ላይ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:52 0:00

XS
SM
MD
LG