በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ አሁኑኑ መላ ልናበጅለት የሚገባ የደህንንነት ጉዳይ ነው


የዩናይትድ ስቴትስ (United States) ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ የአየር ንብረት ለውጥ “አሁኑኑ መፍቲሄ ሊገኝበት የሚገባ ወሳኝ የኢኮኖሚና የጸጥታ ጉዳይ ነው ብለዋል።

“የአለም የአየር ሙቀት አሁን በምናየው ፍጥነት እንዲቀጥልና የባህር ጠለልም በአሁን ፍጥነት ከፍ እንዲል ከተውናቸው የኢኮኖሚና ወታደራዊ ይዞታችንን ለህዝባችን እደገት ሳይሆን እየተለወጠ የሚሄደው መሬት ከሚይስከትለው አንደምታ ጋር በመራምድ ተግባር ላይ ለመዋል እንገደዳለን” ሲሉ ፕረዚዳንቱ አስገንዝበዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማ ዛሬ ይህን ያሉት ከፓሪስ ወጣ ብሎ በሚካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። ጉባኤው የአለም ሙቀት ከሁለት ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ እንዳይሄድ ለማድረግ የሚያስችል አሳሪ የሆነ እርምጃ ለመውሰድ ስምምነት ላይ ለመድረስ እየሞከረ ነው።

የዋይት ሃውስ ቤተመንግስት ዘሬ ባስታወቀው መሰረት 73 የዩናይትድ ስቴትስ (United States) ኩባንያዎች የአየር ንብረት ለውን በሚመለከት የሚወሰድ እርምጃን ለመደገፍ ቃል ገብተዋል። ኮርፐረሽኖች የበካይ ጋዝ ልቀትን በ 50 ከመቶ፣ የውሀ አጠቃቀማቸውን በ 80 ከመቶ እንዲቀንሱ፣ የሚጠቀሙት ኤነርጂ ደግሞ ርኒወብል (renewable) ወይም ከተፈጥሮ ሃብት የሚገኝ እንዲሆን ነው ግቡ የሚጠይቀወ።

የፈረንሳዩ ፕረዚዳንት ፍራንሷ ሆላንድ ደግሞ የአፍሪቃ ሃገሮች ርኒወብል (renewable) ኤነርጂ ወይም ነፋስንና በከርሰ ምድር የሚገኙ የኤነርጂ ምንጮችን ለመጠቅም እንዲችሉ ፈረንሳይ በቀጣዮቹ አራት አመታት ውስጥ $2.1 ቢልዮን ዶላር እንደምትሰጣቸው አስታውቀውል። ዘጋብያችን ሊሳ ብራያንት ከፓሪስ የላከችውን ዘገባ ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ አሁኑኑ መላ ልናበጅለት የሚገባ የደህንንነት ጉዳይ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:05 0:00

XS
SM
MD
LG