ዋሽንግተን ዲሲ —
ቻድ ሐይቅ ሰፊና ብዙ ጥቅም ይሰጥ የነበረ የተፈጥሮ ሃብት ነው፡፡
ይሁን እንጂ ቻድ ሐይቅ ከአጠቃላዩ የውኃው መጠን ባለፉት ሃምሣ ዓመታት ውስጥ ዘጠና ከመቶ የሚሆነውን አጥቷል።
የስድስቱ የቻድ ባህር ተፋሰስ ሀገሮች ኮሚሺን አባላት ጠበብት ሐይቁን ከመጥፋት ለማዳን በሚያስችል ሃሣብ ላይ ለመነጋገር ካመሩን ውስጥ ተሰብስበዋል።
የሚያቀርቡት ሃሳብ ከጥቂት ሣምንታት በኋላ ፓሪስ በሚደረገው የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ እንደሚቀርብ ተነግሯል፡፡
ተጨማሪ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ፡፡