በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪቃ በፓሪሱ የዓየር ንብረት ጉባኤ

“ቀድሞ የአምስት ሜትሮች ጥልቀት የነበረው የቻድ ሃይቅ ዛሬ ከአንድ እስከ አንድ ነጥብ አምስት ሜትር ጥልቀት ብቻ ነው ያለው። የሰው ልጆች አንዳች ሁነኛ እርምጃ በአፋጣኝ ተግባር ላይ እንዲያውሉ የሚጠይቅ የክፍለ ዘመኑ የከፋ ውድመት እየደረሰ ያለው።” የቻዱ ፕሬዝዳንት ኢድሪስ ዴቢ ናቸው። የዓየር ንብረት መዛባት ባስከተለው ጉዳት ክፉኛ እየተራቆተ ስላለው የቻድ ሃይቅ ከተናገሩት የተወሰደ።

ወደ ከባቢ ዓየር የሚለቀቀውን የካርቦን መጠን ለመቀነስ የሚያስችሉ ሁነኛ እርምጃዎችን ለመውሰድ የዓለም መሪዎች ያሳዩትን ቁርጠኝነት ከጅምሩ ያመላከተው የፓሪሱ በዓየር ንብረት ለውጥ ላይ ያተኮረ ጉባኤ ሦሥተኛ ቀኑን ይዟል።

ሁለት መቶ የሚጠጉ አገሮች ልዑካን በተገኙበት ጉባኤ የከባቢ ዓየር ግለትን ለመቀነስ ጠበቅ ያለው ምክክር ደርቷል።

የፈተናውን አሳሳቢነት አስመልክቶ የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ጉባኤውን ተሰናብተው ከመሄዳቸው አስቀድሞ በሰጡት አስተያየት የዓየር ንብረት ለውጥ የዓለማችን የምጣኔ ሃብትና የጸጥታ አደጋ ነው፤ ብለዋል።

ይበልጡን በአፍሪቃ የተፈጥሮ አከባቢ ይዞታ ዙሪያ በተነጣጠሩ ውይይቶች የተመላውን የትላንቱን የጉባኤውን ውሎ የቃኘውን ዘገባ ዝርዝር ከዚህ ያድምጡ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:05 0:00

XS
SM
MD
LG