በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአይቮሪ ኮስት የለውጥ ተምሳሌት የሴት የሙዚቃ ባንድ


የአይቮሪኮስት የሙዚቃ ባንድ በወጣት ሴቶች የሙዚቃ ባንድ
የአይቮሪኮስት የሙዚቃ ባንድ በወጣት ሴቶች የሙዚቃ ባንድ

በአይቮሪኮስት (Ivory Coast) ለረጅም ጊዜ በወንዶች ብቻ የተለመደውን የሙዚቃ ባንድ በወጣት ሴቶች የሙዚቃ ባንድ ለመስበር ቀላል አልነበረም። ቤላ ሞንዶ (Bella Mondo) በሚል ስያሜ የሚታወቀው የሴቶች የሙዚቃ ባንድ በአቢጃን ታዋቂ መጠሪያ ሆኗል።

በአቢጃን በሚገኘው ትልቁ የመዝናኛ የምሽት ቤት ቤላ ሞንዶ(Bella Mondo) ከዚህ ቀደም ከነበራቸው የሙዚቃ ተመልካች ቁጥር የበለጠ እየጨመረ መጥቷል። ከአንድ አመት በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ ሙዚቃቸውን ለተመልካች ያስተዋወቁት በዚሁ ነው፤ እስከዛሬም በሳምንት አንድ ቀን በዚሁ ቦታ ሙዚቃ መጫወታቸውን ቀጥለዋል። ቤላ ሞንዶ የሙዚቃ ባንድ የተመሰረተው እ.አ.አ 2007 ዓ.ም ሲሆን በአይቮሪኮስት ከሚገኙት በጣት ከሚቆጠሩት የሴት የሙዚቃ ባንዶች ውስጥ አንዱና የመጀመሪያው ነው። በዚያንጊዜ የሙዚቃ ተማሪ የነበረችውንፕሪስካ አሉን (Prisca Allou) በሙዚቃ ስራ ላይ የነበረ አንድ ሰው የሴቶች የሙዚቃ ባንድ መመስረት እንደሚፈልግ ይጠይቃል።

“ሴቶች ብቻ የተሰባሰቡበት የሙዚቃ ባንድ መመስረት እንደሚፈልግ ነገረኝ፡ ለናቱ ቃል ገብቶላት ነበር። እንደነገረኝ እናቱ የሙዚቃ ባንድ በወንዶች ብቻ መሆን እንደሌለበት ደጋግማ ትነግረው ነበር። ከዛም የሴት ሙዚቀኞችን ለማፈላለግ ማስታወቂያዎችን ማስነገር ጀመርን።”

እናም አሉ (Allou) በሃገር ውስጥ ባሉት ጋዜጦችና የማስታወቂያ ቦታዎች ሁሉ ማስታወቂያን አወጣች።

“ብዙ ቤተሰቦች ይህንን ሃሳብ በመጀመሪያ አልተቀበሉትም። ልጆቻቸውን ወደትምህርት ቤት የሚልኩት ጊታር በየመንገዱ እንዲጫወቱ አይደለም። ሙዚቀኛ መሆን ለሴቶች የማይሆን ነው ብለው በርካታ ወላጆች ያስቡ ነበር። አፍሪካውያን ሴቶች በቢሮ ስራ ላይ ወይም በቤት ውስጥ መሆን ብቻ ነው የሚጠበቅባቸው።”

አሉ (Allou) እንዳለችው ለሙዚቃ ባንዱ የተመረጡት አብዛኛዎቹ ወጣት ሴት ሙዚቀኞች ብቃታቸው ያን ያህል አልነበረም። እነዚህ ጀማሪ ሙዚቀኞች ለአራት አመታት ሙዚቃን ጠንቅቀው እንዲያውቁ ተደርጓል። በርካታ ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች ማስታወቂያውን ሰምተው ተወዳድረው አልፈው ነበር። ብዙዎቹ ግን ተስፋ በመቁረጥ ሲተዉት በመጨረሻ ስምንቱ ብቻ ቀርተዋል። ከዛ በኃላ ነው እንግዲህ አሉና እና ባንዱ የተፈጠሩት።

በቅርቡ በተለያዩ ቦታዎች ሙዚቃዎቻቸውን ማሳየት ይጀምራሉ። በአብዛኛው የሚጫወቷቸው ሙዚቃዎች የተለያየ የሙዚቃ ስልት ስብስብ ነው፤ እንደ ፋንክ፣ ሬጌ እና ፖፕ የሙዚቃ ስልትን ጨምሮ። ብዙ ሰዎች ይህ የሙዚቃ ባንድ ባጭሩ ይቀጫል የሚል አስተሳሰብ ነበራቸው ትላለች የባንዱ አባል የሆነችው የጊታር ተጫዋቿ ክሎቲልድ ብሌ (Clotilde Ble)።

እ.አ.አ 2013 የbella Mondo አባላት በጋራ የመጀመሪያቸው የሆነውን የሙዚቃ አልበም ለማሳተም በቅተዋል። በርካታ ተመልካች በተገኘበት ታላላቅ የራት ግብዣ ላይ እንዲሁም በአውሮፓና በምዕራብ አፍሪካ ሃገሮች ተዘዋውረው ሙዚቃቸውን የማሳየት እድሉን አግኝተዋል።

“ዛሬ ያለምንም መሳቀቅ ሴቶች ልጆች ጊታር በጀርባቸው አዝለው ሲንቀሳቀሱ ወይም ኪቦርድ ይዘው ሳይ ወይንም ከከበሮው ጀርባ የተቀመጡት ሴቶች መሆናቸውን ስመለከት፤ የእኛ ደፍሮ መውጣት ለሌሎች ትልቅ አስተዋፅዎ እንዳደረገ አያለሁ። ለተቀሩት ሴቶች ጥንካሬ መስጠታችን ብቻ ሳይሆን ለኛም ታላቅ ደስታ እንጎናፀፋለን።” ትላለች የሙዚቃ ባንዱ መስራችና አባል የሆነችው ፕሪስካ አሉ። ቤላ ሞንዶ በአሁኑ ጊዜ ሁለተኛ አልበማቸውን በመስራት ላይ ይገኛሉ።

የቪኦኤዋ ኤሚሊ ሎብ (Emilie Lob) የዘገበችውን መስታወት አራጋው አቀናብራዋለች። ሙሉ ዘገባውን ለመስማት ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያዳምጡ።

የአይቮሪ ኮስት የለውጥ ተምሳሌት የሴት የሙዚቃ ባንድ!
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:20 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG