በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቆሎ ተማሪ በአሜሪካ


ፋይል ፎቶ በአሜሪካ የደብረገነት መድሃኒያለም ዘማሪያን
ፋይል ፎቶ በአሜሪካ የደብረገነት መድሃኒያለም ዘማሪያን

በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስትያናት በአሜሪካን ሃገር ተወልደው ላደጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሃይማኖት ትምህርት በተጨማሪ የኢትዮጵያን ባህልና ታሪክ በማስተማር ከፍተኛውን ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያን ቋንቋ፣ ታሪክና ባህል ለበርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አዳጊ ህፃናትንና ወጣቶችን በማስተማር ላይ ከሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት መካከል በሜሪላንድ የሚገኘው የደብረ ገነት መድሃኒያለም ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን አንዱ ነው። በዚሁ ቤተክርስቲያን በምክትል አስተዳዳሪነትና በቅዳሴ በማገልገል ላይ የሚገኙት መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ገብረወልድ አገዝ ወደ ቤተክርስቲያኒቱ የሚመጡትን በርካታ አዳጊ ሕፃናትን የሃይማኖት ትምህርት ጨምሮ የኢትዮጵያን ታሪክና ቋንቋን በማስተማር ላይ ይገኛሉ።

በአሁኑ ስዓት ትምህርቱን በመከታተል ላይ የሚገኙት አዳጊ ሕፃናቶች እድሜያቸው ከ6-16 አመት ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 3ቱ ከኢትዮጵያ የድቁና ማዕረግን እስከመቀበል ደርሰዋል። መልአከ ምህረት ቆሞስ አባ ገብረወልድ አገዝንና የሚያስተምሩዋቸው አዳጊ ሕጻናት ከመስታወት አራጋው ጋር ቆይታን አድርገዋል። ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ያዳምጡ።

የቆሎ ተማሪ በአሜሪካ!
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:24 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG