ዋሽንግተን ዲሲ —
የዘፈነቻቸው ዜማዎች በተለይም ‘አተረማመሰው’፣ ’በለው በለው’ እና ‘አራዳ’ የተባሉት ዜማዎች በአድማጭ ተወዳጅ በመሆናቸው በተለያዩ የኢትዮጵያ ድምፃውያን ዘንድ ተደጋግመው ተዘፍነዋል። ከዚህ ቀደም በሰራቻቸው ሦስት የሙዚቃ አልበሞች በርካታ አድናቂዎችን አትርፋለች ባሳለፍነው ወር መጨረሻ አራተኛዋ የሆነውን አዲስ የሙዚቃ አልበም ለአድማጭ አቅርባለች። አለም ከበደን በአዳዲስ ስራዎች ቶሎ ቶሎ ያላየናት ለምንድነው?
በሙዚቃ ህይወቷ ዙሪያ ከመስታወት አራጋው ጋር አጭር ቆይታ አድርጋለች። ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ሙሉ ጨዋታውን ያዳምጡ።