በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳኑ ውጊያ አደገኛ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ


የሱዳኑ ውጊያ አደገኛ መሆኑን ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:56 0:00

ሱዳን ውስጥ ባለፈው ቅዳሜ ተጀምሮ አራተኛ ቀኑን ያስቆጠረውን ውጊያ በተመለከተ የቪኦኤ የአፍሪካ ክፍል ባልደረቦች ያነጋገሯቸው የካርቱም ነዋሪዎች ሁኔታው እጅግ አደገኛ መሆኑን ገልጸዋል። ውጊያው ነዋሪዎችን ለከፍተኛ ፍርሃት እና ስቃይ እንደዳረገ አመልክተዋል።

ትውልደ ሱዳን አሜሪካዊው ጋዜጠኛ ኢስማኤል ሹክሹክ ካርቱም ውስጥ የሚኖርበት ህንጻ ከባድ ውጊያ የሚካሄድበት አካባቢ መኾኑን ገልጿል። ብቅ ብሎ ሁኔታውን በምስል ለመቅረጽ እንኳን ህንጻው ላይ አነጣጣሪ ተኳሾች ስላሉ አስጊ መኾኑን አመልክቷል።

ሱዳን ውስጥ የሕዝባዊ ተቃውሞ አንቂዎችን የሚያስተባብረው ኮሚቴ አባሏ የካርቱም ነዋሪ ሙና አል ታሂርም ቀን እና ሌሊት የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማ እና ከቤተ ሰዎቻቸው ጋራ ቤት ዘግተው እንደተቀመጡ ገልጸዋል።

በውጊያው ምክንያት የከተማዋ ነዋሪዎች መደብሮች በመዘጋታቸው በተለይ በዚህ የረመዳን ጾም ወቅት ለከባድ ችግር መጋለጣቸውን ገልጸዋል።

“ሁለቱ ወታደራዊ መሪዎች ካርቱም ጎዳና ላይ ለመፋለም መወሰናቸው ሲቪሉን ሕዝብ አሳዝኗል” ያሉት ሙና አል ታሂር "ይህ የሱዳን ሲቪል ሕዝብ ጦርነት አይደለም። የሱዳን ሕዝብ የሚፈልገው ሰላም፥ ዲሞክራሲ፥ ብልጽግና እና ሲቪል መንግሥት እንዲመሰረትለት ነው" ብለዋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG