በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን የአሜሪካና የአውሮፓ ዲፕሎማቶች ጥቃት


የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር አንተኒ ብሊንከን
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር አንተኒ ብሊንከን

በሱዳን አንድ የአሜሪካ የዲፕሎማቶችን የያዘ አጀብ ትናንት ሰኞ ጥቃት እንደተፈጸመበት የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ አስታውቀዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ከፈጥኖ ደራሽ ኃይል ወይም አር ኤስ ኤፍ ጋር ግንኙነት ባላቸው ኃይሎች መሆኑንም ብሊንከን ጠቁመዋል።

አጀቡ በግልጽ ምልክት የተደረገበት መሆኑን ብሊንከን ለዜና ሰዎች ተናግረዋል።

ከሱዳን ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጄነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን እና ከ አር ኤስ ኤፍ መሪ ጀነራል ሞሃመድ አምዳን ደጋሎ ወይም ኽመቲ ጋር ዛሬ ማለዳ መነጋገራቸውንም ብሊንከን አስታውቀዋል።

“በአሜሪካ ዲፕሎማቶች ላይ የሚጋረጥ ማንኛውም አደጋ ተቀባይነት የለውም” ሲሉ ብሊንከን ለሁለቱ ጀነራሎች መናገራቸውን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

በተመሳሳይ የአውሮፓ ኅብረት ተወካይ መኖሪያ ቤትና የኖርዌይ አምባሳደር መኖሪያ ቤት ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ታውቋል።

ጥቃቶቹ በሱዳን እየተካሄደ ያለው ግጭት ወደ ከፋ ደረጃ ማምራቱን የሚያመላክቱ መሆናቸውን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ ጥቁሟል።

XS
SM
MD
LG