በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግብጽ ወታደሮች ሱዳን ውስጥ ተያዙ


የግብፅ ፕሬዚደንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ትናንት ማምሻውን ከግብጽ ከፍተኛ ወታደራዊ ም/ቤት ጋር ስብሰባ የተቀመጡት/ ፎቶ ሮይተርስ ከላከው ቪዲዮ ላይ በስክሪን ቅጂ የተወሰደ
የግብፅ ፕሬዚደንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ትናንት ማምሻውን ከግብጽ ከፍተኛ ወታደራዊ ም/ቤት ጋር ስብሰባ የተቀመጡት/ ፎቶ ሮይተርስ ከላከው ቪዲዮ ላይ በስክሪን ቅጂ የተወሰደ

ሱዳን ውስጥ የተያዙት የግብጽ ወታደሮች፣ በዚያ የተገኙት ሱዳን አቻዎቻቸው ጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ እንጂ ፤ የትኛውንም ወገን ለመደገፍ አለመኾኑን የግብፅ ፕሬዚደንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ትላንት አስታወቁ።

ከሱዳን ሠራዊት ጋር እየተዋጋ ያለው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ወይም በምጻረ ቃሉ አር ኤስ ኤፍ ፣ “እጅ የሰጡ የግብጽ ወታደሮች ናቸው” ያላቸውን ሠዎች በቪዲዮ አሳይቷል። ወታደሮቹ እጅ ሰጡ የተባለው በስተሰሜን በምትኘው የሜሮው ከተማ መኾኑም ታውቋል።

በሱዳን ዛሬ አራተኛ ቀኑን በያዘውና ተጎጂዎችን ለማንሳት የ24 ሠዓት ተኩስ ማቆም ስምምነት ተደርሶበታል በተባለው ግጭት 185 የሚሆኑ ሰዎች እንደሞቱና 1ሺሕ 800 እንደተጎዱ በመዘገብ ላይ ነው።

ትናንት ማምሻውን ከግብጽ ከፍተኛ ወታደራዊ ም/ቤት ጋር ስብሰባ የተቀመጡት አል-ሲሲ፣ የወታደሮቹን ደህንነት በተመለከተ ከአር ኤስ ኤፍ ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን አስታውቀዋል።

የግብጽ ወታደሮቹ ደህንነታቸው የተጠበቀና ሠራዊታቸው ምግብና ውሃ እንደሚያቀርብላቸው እንዲሁም ወደ አገራቸው ለመመለስ ዝግጁ እንደሆኑ ‘ኽመቲ’ በመባል የሚታወቁት የ አር ኤስ ኤፍ መሪ እና የአብደል ፈታህ አል ቡርሃን ተቀናቃኝ ጀነራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ለስካይ ኒውስ አራቢያ ቲቪ ተናግረዋል።

አል-ሲሲ በተጨማሪም የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ለማበረታታት ግብጽ ከሱዳን ሰራዊትና ከአር ኤስ ኤፍ ጋር በተደጋጋሚ እየተነጋገረች መሆኑን አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG