በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጉቴሬዥ በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ውጊያ አወገዙ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ውጊያ አውግዘው፣ ተፋላሚ ወገኖቹ በአስቸኳይ ግጭቱን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ጸጥታን እንዲያሰፍኑ እና ውይይት እንዲጀምሩም ዋና ጸሃፊው ጥሪ አድርገዋል፡፡

ሁኔታው ሲቪሎችን ጨምሮ አሰቃቂ የሰው ሕይወት መጥፋት እንዳስከተለ የተናገሩት ጉቴሬዥ፣ ግጭቱ የሚቀጥል ከሆነ ለአገሪቱም ሆነ ለቀጠናው አውዳሚ ይሆናል ብለዋል፡፡ በሱዳን ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ ወትሮውንም አስከፊ ነበር ያሉት ዋና ጸሃፊ፣ በሲቪሎችና በረድኤት ድርጅት ሠርራተኞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ እና ዘረፋ አውግዘዋል፡፡

ሁሉም ወገኖች ዓለም አቀፍ ሕግን እንዲያከብሩ እንዲሁም የተመድንና የሌሎችንም ሰራተኞች ደህንነት እንዲያከብሩ ጠይቀዋል፡፡

ከሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች መሪዎች ጋር በሳምንቱ መጨረሻ መነጋገራቸውን ያወሱት ዋና ጸሃፊው፣ ከአፍሪካ ኅብረት፣ ከዓረብ ሊግ እንዲሁም ከአካባቢው አገሮች መሪዎች ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የተመድ ከሱዳን ሕዝብ ጎን እንደሚቆምና፣ የዲሞክራሲ ሽግግሩን መልሶ ለመቀጠል እንዲሁም ሠላምን ለመገንባት የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚደግፍ ዋና ጸሃፊው ጨምረው ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG