በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ እና እንግሊዝ የሱዳን ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠየቁ


የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄምስ ክሌቨርሊ
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄምስ ክሌቨርሊ

የዩናይትድ ስቴትስ እና የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ በሱዳን እየተካሔደ ያለው የእርስ በርስ ውጊያ እንዲቆም ጥሪ አደረጉ፡፡

በዓለም እየተካሔዱ ባሉ ቀውሶች ላይ ለመነጋገር ጃፓን የሚገኙት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንና የእንግሊዙ አቻቸው ጄምስ ክሌቨርሊ ጥሪውን ያስተላለፉት፣ በሱዳን፣ በኹለት ተቀናቃኝ ጄኔራሎች በሚታዘዙ ኃይሎች መሀከል ግጭቱ ለሦስተኛ ቀን በቀጠለበት ኹኔታ ነው፡፡

በካርቱም፣ በአቅራቢያዋ በምትገኘው ኦምዱርማንና በሌሎችም ቁልፍ ቦታዎች፣ የጦር አውሮፕላኖችን ጨምሮ በከባድ መሣሪያዎች የታገዘ ውጊያ በመካሔድ ላይ ነው፡፡

የሱዳን ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጀነራል አብዱል ፈታሕ አል ቡርሃንና የፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪ ኃይል ወይም በምጻሕረ ቃሉ አርኤስኤፍ በሚል የሚጠራው ኃይል አዛዥ የኾኑት ጀነራል ሞሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ እያንዳንዳቸው፣ በመዲናዋ ካርቱም ብቻ፣ በ10ሺሕ የሚቆጠር ሠራዊት እንዳላቸው ተነግሯል፡፡

በጃፓን የተገናኙት ኹለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ጀነራል አል ቡርሃንና ጀነራል ዳጋሎ ወይም አዘውትረው እንደሚጠሩት ‘ኽመቲ’፣ ግጭቱን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ጠይቀዋል።

ትላንት እሑድ ብቻ፣ 41 ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቱ ሐኪሞች አስታውቀዋል፡፡ ይህም የጠቅላላ ሟቾቹን ቁጥር 97 አድርሶታል፡፡

XS
SM
MD
LG